Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘካርያስ 12:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በዚያን ጊዜ የይሁዳ አለቆች በልባቸው ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አምላካቸው ስለ ሆነ በኢየሩሳሌም የሚኖሩት ሕዝቡ በእርሱ ኀይልን ያገኛሉ’ ይላሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የይሁዳ መሪዎች በልባቸው፣ ‘የኢየሩሳሌም ሕዝቦች ብርቱ ናቸው፤ አምላካቸው የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነውና’ ይላሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የይሁዳም አለቆች በልባቸው፦ “በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ብርታታቸው አምላካቸው የሠራዊት ጌታ ነው” ይላሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የይሁዳም አለቆች በልባቸው፦ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ በአምላካቸው በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ብርታት አለ ይላሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የይሁዳም አለቆች በልባቸው፦ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ በአምላካቸው በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ብርታት አለ ይላሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘካርያስ 12:5
28 Referencias Cruzadas  

መጠጊያዬ እግዚአብሔር ይመስገን! ለሰልፍ ያሠለጥነኛል፤ ለጦርነትም ያዘጋጀኛል።


ብርታትን የሚሰጠኝና መንገዴን የሚያቀናልኝ እግዚአብሔር ነው።


ለጦርነት ኀይልን ትሰጠኛለህ፤ በጠላቶቼም ላይ ድልን ታጐናጽፈኛለህ።


እግዚአብሔር መጠጊያችንና ኀይላችን ነው፤ ችግር በሚደርስብን ጊዜ ሁሉ ረዳታችን ነው።


እናንተ የሰዶም ገዢዎች ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እናንተ የገሞራ ሕዝብ ሆይ! የአምላካችንን ትምህርት አድምጡ፤


መሪዎችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ግብረ አበሮች ሆኑ፤ እያንዳንዱ ሁልጊዜ ገጸ በረከትና ጉቦ ይቀበላል፤ አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች መብት አይጠብቁም፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች አቤቱታ አይሰሙም።


ቀድሞ የነበሩሽን ዐይነት ገዢዎችንና አማካሪዎችን አስነሣልሻለሁ፤ ከዚህ በኋላ ‘እውነት የሚገኝባት ታማኝ ከተማ’ ተብለሽ ትጠሪአለሽ።”


በዚያን ጊዜ የሠራዊት አምላክ ከሞት ለተረፉት ሕዝቡ የክብር አክሊል ይሆናል።


በዳኝነት ለሚያገለግሉት የፍትሕ ጥበብ ይሰጣቸዋል፤ የከተማይቱን የቅጽር በሮች ከጠላት ለሚከላከሉትም ኀይልን ይሰጣቸዋል።


እግዚአብሔር ከባድ እንቅልፍ ስለ ጣለባችሁ እናንተ ነቢያት ዐይኖቻችሁን ጨፍናችኋል፤ እናንተም ባለ ራእዮች አእምሮአችሁን ዘግታችኋል።


በጽድቅ የሚያስተዳድር ንጉሥ የሚነሣበት ጊዜ ይመጣል፤ ሹማምንቱም በትክክል ይፈርዳሉ።


“ ‘ጽድቅና ኀይል የሚገኘው ከእግዚአብሔር ብቻ ነው’ ብለው ስለ እኔ ይናገራሉ፤ የሚጠሉኝ ሁሉ ወደ እኔ መጥተው በዕፍረት ላይ ይወድቃሉ።


“እኔ በነሐስ ፈንታ ወርቅ፥ በብረት ፈንታ ብር፥ በእንጨት ፈንታ ነሐስ፥ በድንጋይም ፈንታ ብረት አመጣለሁ፤ ሰላምን እንደ አስተዳዳሪሽ ጽድቅንም እንደ ገዢሽ አድርጌ እመድባለሁ።


የራሳቸው ወገን ከመካከላቸው ተነሥቶ መሪአቸው ይሆናል፤ እኔ ራሴ ስለማመጣው እርሱ ወደ እኔ ይቀርባል፤ አለበለዚያማ ማን ደፍሮ ሊቀርብ ይችላል?


የያዕቆብና የአገልጋዬን የዳዊትን ዘሮች ትቼአለሁ ማለት ነው፤ ይህም ማለት ለአገልጋዬ ለዳዊት በአብርሃም፥ በይስሐቅና በያዕቆብ ዘሮች ላይ የሚነግሥ አንድም ተወላጅ አላስነሣለትም ማለት ነው። እኔ ግን ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ ንብረታቸውን እመልስላቸዋለሁ።”


እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ በኢየሩሳሌም ሆኖ፥ የሚያስፈራ ድምፁን ያሰማል፤ ሰማይና ምድር ይናወጣሉ፤ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ ለእስራኤል መጠጊያ ምሽግ ይሆናል፤


እኔ አምላካቸው አበረታቸዋለሁ እነርሱም ለቃሌ ይታዘዛሉ።” እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


“እኔ የይሁዳን ሕዝብ ብርቱ አደርጋለሁ፤ የእስራኤልንም ሕዝብ እታደጋለሁ፤ ስለምራራላቸውም ሁሉንም ወደ አገራቸው እመልሳለሁ፤ ከዚህ በፊት ከቶ ጥዬአቸው እንደማላውቅ ይሆናሉ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ስለ ሆንኩ ጸሎታቸውን እሰማለሁ።


በዚያን ጊዜ ፈረሶቻቸውን በፍርሃት አስጨንቃለሁ፤ ፈረሰኞችንም አሳብዳለሁ፤ የጠላቶቻቸውን ፈረሶች አሳውራለሁ፤ የይሁዳን ሕዝብ ግን በዐይኔ እየተመለከትኩ እጠብቃቸዋለሁ።


“በዚያን ጊዜ የይሁዳን ሕዝብ አለቆች በእሳት ማንደጃ ላይ ተከምሮ እንደሚነድ እንጨት፥ በእህል ነዶዎች መካከል እንደ ተቀጣጠለ ችቦ አደርጋቸዋለሁ፤ በአካባቢው ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ ያወድማሉ፤ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ግን ምንም ሳይደርስባቸው በከተማይቱ ውስጥ ይኖራሉ።


የይሁዳ ሰዎች ኢየሩሳሌምን ለመከላከል ይዋጋሉ፤ በዙሪያዋም ያሉትን መንግሥታት ሀብት ሁሉ ማርከው ይወስዳሉ፤ ከሚወስዱትም ምርኮ ወርቅ፥ ብርና የልብስ ዐይነት እጅግ ብዙ ይሆናል።


ልቤ ከእስራኤል የጦር አዛዦች ጋር ነው፤ እንዲሁም ደስ ብሎአቸው በበጎ ፈቃድ ከተነሣሡት ጋር ነው፤ እግዚአብሔር ይመስገን!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos