ዳዊት ወደ ያቤሽ ገለዓድ ሰዎች መልእክተኞችን ልኮ እንዲህ አላቸው፦ “እርሱን በመቅበር ለጌታችሁ ለሳኦል ቸርነትን ስላሳያችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ።
ሩት 2:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናዖሚም “ለሕያዋንና ለሙታን የሰጠውን ተስፋ የሚፈጽም አምላክ ቦዔዝን ይባርከው!” አለች፤ ቀጥላም “ያ ሰው እኮ የቅርብ ዘመዳችን ነው! እንዲያውም ለእኛ ኑሮ የማሰብ ኀላፊነት ካለባቸው ሰዎች አንዱ እርሱ ነው” አለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኑኃሚንም ምራቷን፣ “በጎነቱን ለሕያዋንም ሆነ ለሙታን ማድረጉን ያልተወ እግዚአብሔር ይባርከው” አለቻት፤ ቀጥላም፣ “ሰውየው እኮ የሥጋ ዘመዳችን ነው፤ የመቤዠት ግዴታ ካለባቸው ዘመዶቻችን አንዱ እርሱ ነው” አለቻት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ናዖሚም ምራትዋን፦ “በሕያዋን እና በሙታን ላይ ቸርነቱ የማያልቅበት ጌታ የተባረከ ይሁን” አለቻት። ናዖሚም ደግሞ፦ “ይህ ሰው የቅርብ ዘመዳችን ነው፥ እርሱም ሊቤዡን ከሚችሉት አንዱ ነው” አለቻት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኑኃሚንም ምራትዋን፦ ቸርነቱን በሕያዋንና በሙታን ላይ አልተወምና በእግዚአብሔር የተባረከ ይሁን አለቻት። ኑኃሚንም ደግሞ፦ ይህ ሰው የቅርብ ዘመዳችን ነው፥ እርሱም ሊቤዡን ከሚችሉት አንዱ ነው አለቻት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኑኃሚንም ምራትዋን “ቸርነቱን በሕያዋንና በሙታን ላይ አልተወምና በእግዚአብሔር የተባረከ ይሁን፤” አለቻት። ኑኃሚንም ደግሞ “ይህ ሰው የቅርብ ዘመዳችን ነው፤ እርሱም ሊቤዡን ከሚችሉት አንዱ ነው፤” አለቻት። |
ዳዊት ወደ ያቤሽ ገለዓድ ሰዎች መልእክተኞችን ልኮ እንዲህ አላቸው፦ “እርሱን በመቅበር ለጌታችሁ ለሳኦል ቸርነትን ስላሳያችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ።
ከብዙ ጊዜ በኋላ እንደገና ለእኔ ችግር ማሰብ ስለ ጀመራችሁ በጌታ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል፤ ይህንንም ስል የአሰባችሁትን በሥራ ለማሳየት መልካም አጋጣሚ አላገኛችሁም ነበር ማለቴ ነው እንጂ ስለ እኔ ችግር ማሰባችሁን አቋርጣችኋል ማለቴ አይደለም።
ሴቶች ናዖሚን እንዲህ አሉአት፦ “ዛሬ ወራሽና ጧሪ ያላሳጣሽ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን! እግዚአብሔር ይህን ልጅ በእስራኤል ዝነኛ ያድርገው!
አንተም ስለዚህ ጉዳይ ማወቅ የሚገባህ ይመስለኛል፤ እንግዲህ መሬቱን ከፈለግኸው እዚህ በተቀመጡትና በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊት ለራስህ ልታስቀረው ትችላለህ፤ የማትፈልገው ከሆነ ግን ቊርጡን ንገረኝ፤ መሬቱን የማስቀረት ቅድሚያ ያለህ አንተ ነህ፤ ከአንተም ቀጥሎ እኔ ነኝ።” ሰውየውም “እኔ አስቀረዋለሁ” አለ።