Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 25:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 አንድ እስራኤላዊ ድኻ ሆኖ መሬቱን ለመሸጥ ቢገደድ የቅርብ ዘመዱ የሆነ ሰው ሊዋጅለት ይገባዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “ ‘ከወገንህ አንዱ ደኽይቶ ርስቱን ቢሸጥ፣ የቅርብ ዘመዱ መጥቶ ወገኑ የሸጠውን ይዋጅለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 “ወንድምህም ቢደኸይ ከርስቱም ቢሸጥ፥ የቅርብ ዘመዱ የሆነ ሰው መጥቶ ወንድሙ የሸጠውን ይቤዠዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ወን​ድ​ም​ህም ቢደ​ኸይ፥ ከር​ስ​ቱም ቢሸጥ፥ ለእ​ርሱ የቀ​ረበ ዘመዱ መጥቶ ወን​ድሙ የሸ​ጠ​ውን ይቤ​ዠ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ወንድምህም ቢደኸይ ከርስቱም ቢሸጥ፥ ለእርሱ የቀረበ ዘመዱ መጥቶ ወንድሙ የሸጠውን ይቤዠዋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 25:25
14 Referencias Cruzadas  

“መሬት በሚሸጥበት ጊዜ የቀድሞ ባለቤቱ መልሶ ለመዋጀት መብት ያለው መሆኑ መታወቅ አለበት።


ሊዋጅለት የሚችል የቅርብ ዘመድ ባይኖረው ግን ዘግየት ብሎ ሀብት በሚያገኝበት ጊዜ እርሱ ራሱ መዋጀት ይችላል።


“ምናልባት በመካከልህ የሚኖር አንድ መጻተኛ ባለጸጋ ሲሆን፥ እስራኤላዊ ወገንህ ደኽይቶ ለዚያ መጻተኛ ወይም ከእርሱ ቤተሰብ ለአንዱ ራሱን በባርነት ያስገዛ ይሆናል።


“አንድ ሰው ከሌላ ሰው የገዛውን መሬት ለእግዚአብሔር የተለየ ስጦታ አድርጎ ቢያቀርብ፥


እናንተ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁ፤ እርሱ ምንም እንኳ ሀብታም ቢሆን በእርሱ ድኻ መሆን እናንተ ሀብታሞች እንድትሆኑ ስለ እናንተ ብሎ ድኻ ሆነ።


አዲስ መዝሙርም እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በደምህ ከየነገዱ፥ ከየቋንቋው፥ ከየወገኑ፥ ከየሕዝቡ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ለመዋጀት፥ አንተ ስለ ታረድህ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ ለመውሰድና ማኅተሞቹን ለመክፈት የተገባህ ሆነሃል፤


ናዖሚም “ለሕያዋንና ለሙታን የሰጠውን ተስፋ የሚፈጽም አምላክ ቦዔዝን ይባርከው!” አለች፤ ቀጥላም “ያ ሰው እኮ የቅርብ ዘመዳችን ነው! እንዲያውም ለእኛ ኑሮ የማሰብ ኀላፊነት ካለባቸው ሰዎች አንዱ እርሱ ነው” አለች።


እኔ የቅርብ ዘመድ መሆኔ እውነት ነው፤ ነገር ግን ከእኔ ይልቅ ቅርብ የሆነ ሌላ ዘመድ አለ፤


ስትቃርሚ አብረውሽ የነበሩት ሴቶች የሚያገለግሉት ቦዔዝ የቅርብ ዘመዳችን ነው፤ እነሆ! እርሱ ዛሬ ማታ ገብስ ይወቃል፤


“አንቺ ማን ነሽ?” ብሎም ጠየቃት። እርስዋም “ጌታዬ ሆይ! አገልጋይህ እኔ ሩት ነኝ፤ አንተ የቅርብ ዘመድ ስለ ሆንክ ለእኔ ኑሮ የማሰብ ኀላፊነት አለብህ፤ ስለዚህ ልብስህን ባገልጋይህ ላይ ጣል አለችው።”


ቦዔዝም የቅርብ ዘመድ የሆነውን ሰው እንዲህ አለው፦ “እነሆ ናዖሚ ከሞአብ አገር ተመልሳ መጥታለች፤ የዘመዳችንን የአቤሜሌክንም መሬት መሸጥ ትፈልጋለች፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos