ሮሜ 9:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የእግዚአብሔር ምርጫ የሚገኘው በሰው ፈቃድና በሰው ሥራ ሳይሆን በእግዚአብሔር ምሕረት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ይህ ከሰው ፍላጎት ወይም ጥረት ሳይሆን፣ ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ይህ ለፈለገ ወይም ለሮጠ አይደለም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ለሮጠና ለቀደመ አይደለም፤ እግዚአብሔር ይቅር ላለው ነው እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ምሕረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔን ላልጠየቁኝ ተገለጥኩላቸው፤ ላልፈለጉኝም ተገኘሁላቸው፤ ስሜንም ላልጠራ ሕዝብ ‘እነሆ፥ እዚህ አለሁ፥ እነሆ፥ እዚህ አለሁ’ አልኳቸው።
አባቴ ሁሉን ነገር ሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ ማንም የለም። እንዲሁም ከወልድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም፤ ማንም ወልድ ካልገለጠለት በቀር አብን ሊያውቅ አይችልም።
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በቅዱስ መንፈሱ ተደስቶ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ! ይህንን ነገር ከጥበበኞችና ከዐዋቂዎች ሰውረህ ላልተማሩት ስለ ገለጽክላቸው አመሰግንሃለሁ፤ አዎ፥ አባት ሆይ፥ ይህን ለማድረግ የአንተ በጎ ፈቃድ ሆኖአል።
ነፋስ ወደ ፈለገው አቅጣጫ ይነፍሳል፤ ድምፁንም ትሰማለህ፤ ነገር ግን ከየት እንደሚመጣና ወዴትም እንደሚሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው።”
የሄድኩትም እግዚአብሔር በገለጠልኝ መሠረት ነው። ከዚህ በፊት የሠራሁትም ሆነ አሁን የምሠራው ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር በማለት ለአሕዛብ የምሰብከውን ወንጌል ታላላቅ ለሆኑት መሪዎች በግል አስታወቅኋቸው።