Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 65:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔን ላልጠየቁኝ ተገለጥኩላቸው፤ ላልፈለጉኝም ተገኘሁላቸው፤ ስሜንም ላልጠራ ሕዝብ ‘እነሆ፥ እዚህ አለሁ፥ እነሆ፥ እዚህ አለሁ’ አልኳቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “ላልጠየቁኝ ራሴን ገለጥሁላቸው፤ ላልፈለጉኝ ተገኘሁላቸው። ስሜን ላልጠራ ሕዝብ፣ ‘አለሁልህ፤ አለሁልህ’ አልሁት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ላልጠየቁኝ ተገለጥሁ፥ ላልፈለጉኝም ተገኘሁ፤ በስሜም ያልተጠራውን ሕዝብ፦ “አለሁኝ፥ አለሁኝ” አልኩት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ያል​ፈ​ለ​ጉኝ አገ​ኙኝ፤ ላል​ጠ​የ​ቁ​ኝም ተገ​ኘሁ፤ ስሜን ላል​ጠራ ሕዝብ፥ “እነ​ሆኝ” አል​ሁት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ላልጠየቁኝ ተገለጥሁ፥ ላልፈለጉኝም ተገኘሁ፥ በስሜም ያልተጠራውን ሕዝብ፦ እነሆኝ፥ እነሆኝ አልሁት።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 65:1
20 Referencias Cruzadas  

እርሱም ወደ ኋላ መለስ ሲል እኔን አየኝና ጠራኝ፤ እኔም ‘ጌታዬ፥ እነሆ አለሁ!’ አልኩት፤


እስከ ምድር ዳርቻ ያሉ ሰዎች ሁሉ አስታውሰው ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ፤ በዓለም የሚገኙት ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ።


በዚያን ጊዜ የእሴይ (የዳዊት) ዘር ለሕዝቦች ምልክት ሆኖ ይቆማል፤ ሕዝቦች እርሱን ይፈልጉታል፤ መኖሪያውም የተከበረ ይሆናል።


ለጽዮን መልካም ነገርን የምታበሥሩ ሆይ! ወደ ከፍተኛ ተራራ ውጡ! እናንተ ለኢየሩሳሌም መልካም ዜናን የምታበሥሩ ሆይ! ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ! ጮክ በሉ አትፍሩ! ለይሁዳ ከተሞች፥ “እነሆ፥ አምላካችሁ” በሉ።


በመጀመሪያ ይህን ዜና ለጽዮን የገለጥኩላት እኔ ነኝ፤ ለኢየሩሳሌምም መልካም ዜና አብሣሪ የላክሁላት እኔ ነኝ።


የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! የፈጠራችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የታደግኋችሁ ስለ ሆነ አትፍሩ፤ እናንተ የእኔ ናችሁ፤ በስማችሁም ጠርቼአችኋለሁ።


“ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ ስለሌለ፥ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ያላችሁ ሁሉ ወደ እኔ ተመልሳችሁ ደኅንነትን አግኙ።


እኔ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር አምላክህ ስላከበርኩህ እነሆ፥ የማታውቃቸውን ሕዝቦች ትጠራለህ፤ የማያውቁህም ሕዝቦች ወደ አንተ ይፈጥናሉ።”


እኛ በአንተ እንዳልተገዙና በስምህ እንዳልተጠሩ ወገኖች ከሆንን ብዙ ጊዜአችን ነው።


የእስራኤል ሕዝብ ብዛት ሊቈጠር ወይም ሊለካ እንደማይቻል የባሕር አሸዋ ይሆናል፤ አሁን እግዚአብሔር “ሕዝቤ አይደላችሁም” ቢላቸው በዚሁ ስፍራ “የሕያው እግዚአብሔር ልጆች!” ተብለው የሚጠሩበት ጊዜ ይመጣል፤


በዚያን ጊዜ ብዙ የአሕዛብ ነገዶች ከእግዚአብሔር ጋር ተባብረው ወገኖቹ ይሆናሉ። እርሱም በመካከላችሁ ይኖራል፤ እኔንም ወደ እናንተ የላከኝ እርሱ መሆኑን ትገነዘባላችሁ።


ኢየሱስ ባያት ጊዜ ጠራትና “አንቺ ሴት ከበሽታሽ ተፈውሰሻል!” አላት።


በማግስቱ ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ “እነሆ፥ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ይህ ነው!


ኢሳይያስም፦ “ላልፈለጉኝ ተገኘሁ፤ ‘እግዚአብሔር የት ነው?’ ብለው ላልጠየቁኝም ተገለጥሁ፤” በማለት ደፍሮ ተናግሮአል።


እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፤ ይህም ጽድቅ ከእምነት የሚገኘው ነው።


እናንተ ቀድሞ የእግዚአብሔር ሕዝብ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ ናችሁ፤ ቀድሞ ምሕረት አላገኛችሁም ነበር፤ አሁን ግን ምሕረት አግኝታችኋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos