ሮሜ 16:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በክርስቶስ መሆኑ ተፈትኖ ለተመሰከረለት ለአጴሊስ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ ከአርስጦቡሎስ ቤተሰብ ለሆኑትም ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በክርስቶስ ያለው እምነቱ ተፈትኖ ለተመሰገነው ለኤጤሌን ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከአርስጣባሉ ቤተ ሰብ ለሆኑትም ሰላምታ አቅርቡልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በክርስቶስ መሆኑ ተፈትኖ ለተመሰገነው ለአፕሊን ሰላምታ አቅርቡልኝ። የአሪስቶቡሉ ቤተሰብ ለሆኑት ሰላምታ አቅርቡልኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በክርስቶስ የተመረጠውን ኤጤሌንን ሰላም በሉ፤ እነ አርስጠቦሎስንም ሰላም በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በክርስቶስ መሆኑ ተፈትኖ ለተመሰገነው ለኤጤሌን ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከአርስጣባሉ ቤተ ሰዎች ላሉት ሰላምታ አቅርቡልኝ። |
ከእኔ ጋር ታስረው ለነበሩና በሐዋርያትም መካከል ታዋቂዎች ለነበሩት አይሁድ ዘመዶቼ፥ ለአንድሮኒቆስና ለዩኒያስ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ እነርሱ በክርስቶስ በማመን እኔን ይቀድሙኛል።
ኢየሱስን ከሞት ያስነሣው የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችሁ ቢኖር ኢየሱስ ክርስቶስን ከሞት ያስነሣው አምላክ በውስጣችሁ በሚኖረው መንፈሱ አማካይነት ለሟች ሥጋችሁ ሕይወትን ይሰጠዋል።
የክርስቶስ የሆነ አንድ ሰው ዐውቃለሁ፤ ይህ ሰው ከዐሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ተወሰደ፤ (የተወሰደውም ከነሥጋው ይሁን ወይም አይሁን አላውቅም፤ እግዚአብሔር ያውቃል።)
ብዙ ጊዜ በብዙ መንገድ ተፈትኖ ትጉህ ሆኖ የተገኘውን ወንድማችንን ከነቲቶ ጋር የላክነውም በዚሁ ምክንያት ነው፤ እርሱ በእናንተ ላይ ያለው እምነት ትልቅ ስለ ሆነ አሁን በዚህ ሥራ ለመርዳት ያለው ትጋት ከምንጊዜውም የበለጠ ነው።
አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትእዛዞች ስለ መጠበቅህ በልብህ ያለውን ሐሳብ ያውቅ ዘንድ አንተን ለመፈተን በዚህ በረሓ አርባ ዓመት ሙሉ በመከራ ውስጥ በማሳለፍ እንዴት እንደ መራህ አስታውስ።
ጢሞቴዎስ፥ ታማኝነቱ ተፈትኖ የተመሰከረለት መሆኑንና ከእኔም ጋር እንደ አባትና ልጅ ተባብረን ወንጌልን በማስተማር አብረን ስንሠራ መቈየታችንን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።
ይህ ፈተና የሚደርስባችሁ የእምነታችሁን እውነተኛነት ለማረጋገጥ ነው፤ የሚጠፋ ወርቅ እንኳ በእሳት ይፈተናል፤ ከወርቅ ይልቅ የከበረ እምነታችሁ እንደዚሁ መፈተን አለበት፤ ይህም የተፈተነ እምነታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፥ ክብርንና ውዳሴን ያስገኝላችኋል።