መዝሙር 97:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መብረቁ በዓለም ላይ ያበራል፤ ምድርም አይታ ትንቀጠቀጣለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መብረቁ ዓለምን አበራ፤ ምድርም አይታ ተንቀጠቀጠች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መብረቆቹ ለዓለም አበሩ፥ ምድር አየችና ተናወጠች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ አመስግኑ፥ ደስም ይበላችሁ፥ ዘምሩም። |
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን እውነተኛ አምላክ ነህ፤ አንተ ሕያው አምላክ፥ ዘለዓለማዊ ንጉሥ ነህ፤ አንተ በምትቈጣበት ጊዜ ዓለም ይናወጣል፤ የአሕዛብ መንግሥታትም የአንተን ቊጣ ችለው አይቆሙም።
በሰማይ ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ተከፈተ፤ የእርሱም የኪዳን ታቦት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ታየ። መብረቅ፥ ድምፅ፥ ነጐድጓድ፥ የምድር መናወጥና ታላቅም በረዶ ሆነ።
ከዚህ በኋላ ሰማይ ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆ፥ ነጭ ፈረስም አየሁ፤ በፈረሱ ላይ የተቀመጠው ታማኝና እውነተኛ የሚባል ነው፤ እርሱ በትክክል ይፈርዳል፤ ይዋጋልም፤