በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሴትም አደርጋለሁ፤ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ለስምህ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ።
በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አደርጋለሁ፤ ልዑል ሆይ፤ ስምህን በመዝሙር እወድሳለሁ።
አቤቱ፥ በሙሉ ልቤ አመሰግንሃለሁ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግራለሁ።
በአንተ ደስ ይለኛል፥ ሐሤትንም አደርጋለሁ፤ ልዑል ሆይ፥ ለስምህ እዘምራለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! በሙሉ ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ በመላእክት ፊት ለአንተ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ።
የምስጋና መዝሙር እየዘመርኩ፥ የአንተን ድንቅ ሥራዎች ሁሉ እናገራለሁ።
አሁን ግን በከበቡኝ ጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ አደረግሁ፤ በደስታ “እልል” እያልኩ በመቅደሱ ውስጥ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ እየዘመርኩም እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
እግዚአብሔር ኀይሌና ጋሻዬ ነው፤ ስለሚረዳኝና ደስ ስለሚያሰኘኝም በእርሱ እተማመናለሁ፤ በመዝሙሮቼም አመሰግነዋለሁ።
አምላክ ሆይ! ከዚያም በኋላ ለአንተ ለምታስደስተኝ ወደ መሠዊያህ ሄጄ እሰግድልሃለሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ በገናዬን እየደረደርኩ አመሰግንሃለሁ።
በአንተ ከለላ ሥር ያሉ ሁሉ ይደሰቱ፤ ለዘለዓለምም እልል ይበሉ የአንተን ስም የሚወዱትን ሁሉ በደስታም እንዲፈነድቁ ከልላቸው።
ስለ እውነተኛነቱ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ ለልዑል አምላክ ስም የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ።
በምድር ሁሉ ላይ ጌታና ሁሉን ቻይ አምላክ አንተ እግዚአብሔር እንደ ሆንክ ይወቁ።
ጌታ አምላኬ ሆይ! በሙሉ ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ስምህንም ለዘለዓለም አከብራለሁ።
ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! አንተን ማመስገንና የምስጋና መዝሙር ለአንተ ማቅረብ መልካም ነው።
እግዚአብሔር ሆይ፥ የአንተ ታላላቅ ሥራዎች ደስ ያሰኙኛል፤ አንተ ስላደረግኻቸውም ነገሮች በደስታ እዘምራለሁ።
በሕዝቦች መካከል ክብሩን አስታውቁ፤ ለሕዝቦችም ሁሉ ታላቅ ሥራውን አውሩ!
እግዚአብሔር ስላደረገው ነገር ጻድቃን ሁሉ ደስ ይበላችሁ! ቅዱስ ስሙንም አመስግኑ!
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ በምድር ሁሉ ላይ ልዑል አምላክ ነህ፤ ሐሰተኞች አማልክት ሁሉ በሥልጣንህ ሥር ናቸው።
“ንጉሥ ሆይ! ልዑል እግዚአብሔር ለአባትህ ለናቡከደነፆር ንጉሥነትንና ታላቅነትን፥ ክብርንና ገናናነትን ሰጠው፤
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜም “ደስ ይበላችሁ!” እላለሁ።