መዝሙር 9:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በእውነተኛ ፍርዱ ተገለጠ፤ ክፉ ሰዎችም በክፉ ሥራቸው ወጥመድ ተያዙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በትክክለኛ ፍርዱ የታወቀ ነው፤ ክፉዎችም በእጃቸው ሥራ ተጠመዱ። ሒጋዮን ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሕዛብ በሠሩት ጉድጓድ ወደቁ፥ በዚያችም በሸሸጓት ወጥመድ እግራቸው ተጠመደች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ፍርድን ማድረግ ያውቃል፤ ኀጢአተኛው በእጆቹ ሥራ ተጠመደ። |
እግዚአብሔር በእንዴት ያለ ታላቅ ኀይል ግብጻውያንን እንዳሸነፈ እስራኤላውያን ባዩ ጊዜ እግዚአብሔርን ፈሩ፤ በእግዚአብሔርና በአገልጋዩ በሙሴ አመኑ።
እኔም ልቡን ስለማደነድነው ያሳድዳችኋል፤ ስለዚህም በንጉሡና በሠራዊቱ ላይ የምጐናጸፈው ድል ለእኔ ክብር ይሆናል፤ በዚያን ጊዜ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።” እስራኤላውያንም እንደ ተነገራቸው አደረጉ።
በዚህ ዐይነት የኀይል ክንዴን በእነርሱ ላይ አንሥቼ እስራኤላውያንን ከአገራቸው በማወጣበት ጊዜ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”
እግዚአብሔር ፊደል በፊደል ላይ፥ መስመር በመስመር ላይ፥ ትምህርት በትምህርት ላይ እያነባበረ ሊያስተምራችሁ የፈቀደው ስለዚህ ነው፤ በዚያን ጊዜ በእርምጃችሁ ሁሉ ትሰናከላላችሁ፤ ትቈስላላችሁ፤ በወጥመድም ተይዛችሁ ትታሰራላችሁ።
ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳርዮስ በየአገሩ ለሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ ነገዶች በጽሑፍ እንዲህ የሚል መልእክት አስተላለፈ፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!
አዶኒቤዜቅም “የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡባቸው ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ ሥር ፍርፋሪ እየለቀሙ ይበሉ ነበር፤ በእነርሱ ላይ የፈጸምኩትን ግፍ ዛሬ እግዚአብሔር በእኔ ላይ መልሶ አመጣብኝ” ሲል ተናገረ። ወደ ኢየሩሳሌምም ተወስዶ በዚያው ሞተ።
በዚህች ቀን እግዚአብሔር በአንተ ላይ ድልን ያጐናጽፈኛል፤ እኔም ራስህን እቈርጣለሁ፤ የፍልስጥኤማውያንንም ወታደሮች ሥጋ ለአሞራዎችና ለአራዊት ምግብ አድርጌ እሰጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ መላው ዓለም በእስራኤል ዘንድ አምላክ እንዳለ ያውቃል።