መዝሙር 85:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ያበለጽገናል፤ ምድራችንም ብዙ የመከር ፍሬ ትሰጠናለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በጎ ነገር ይለግሳል፤ ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እውነት ከምድር በቀለች፥ ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ። ለዘለዓለምም ስምህን አከብራለሁ፤ |
በምድሩ ላይ በቂ እህል ይኑር፤ ተራራዎች በሰብል ይሸፈኑ፤ እንደ ሊባኖስ ተራራዎችም ፍሬያማ ይሁኑ፤ የእህሉም ነዶ እንደ ሣር የበዛ ይሁን።
ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ እንደ ፀሐይና እንደ ጋሻ ነህ፤ በቸርነትና በክብር ትጠብቀናለህ፤ ደግ ለሚሠሩ ሰዎች ማናቸውንም መልካም ነገር አትከለክላቸውም።
ነገር ግን እግዚአብሔር መንፈሱን በእኛ ላይ የሚያፈስበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ምድረ በዳው ለም ይሆናል፤ ለሙም መሬት ብዙ ፍሬ ይሰጣል።
እናንተ ከላይ ያላችሁ ሰማያት! ጽድቅን እንደ ዝናብ አውርዱ፤ ደመናም ያርከፍክፈው፤ ምድር ትከፈት፤ ደኅንነትም ያቈጥቊጥ፤ እኔ እግዚአብሔር የፈጠርኩት ስለ ሆነ ጽድቅም ከእርሱ ጋር ይብቀል።”
እግዚአብሔር መልካም የሆነውንና ከአንተ የሚፈልገውን ነግሮሃል፤ ይኸውም ፍትሕን እንድትጠብቅ፥ ደግነትን እንድትወድ፥ ከአምላክህ ጋር በትሕትና እንድትመላለስ ነው።
እህላቸውን በሰላም ዘርተው ፍሬውን ይሰበስባሉ የወይን ተክሎቻቸውም ያፈራሉ። በቂ ዝናብ ስለሚዘንብ ምድሪቱ ብዙ ሰብል ትሰጣለች፤ ከስደት ለተረፉት ሕዝብ ይህን ሁሉ በረከት እሰጣለሁ።
በመልካም መሬት ላይ የተዘራው የሚያመለክተው፥ ቃሉን ሰምቶ በማስተዋል የሚቀበለውን ሰው ነው፤ እርሱ ፍሬ ያፈራል፤ አንዱ መቶ፥ አንዱ ሥልሳ፥ አንዱ ሠላሳ ፍሬ ይሰጣል።”
ይህን በሰሙ ጊዜ ሁሉም ጌታን አመሰገኑ፤ ጳውሎስንም እንዲህ አሉት፦ “ወንድም ሆይ! በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ ምእመናን በአይሁድ መካከል እንዳሉና ሁሉም ለሕግ ቀናተኞች እንደ ሆኑ ታውቃለህ፤
እናንተን ግን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አደረገ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ጥበባችን፥ ጽድቃችን፥ ቅድስናችንና ቤዛችን እንዲሆን አደረገው።
መልካም ስጦታና ፍጹም በረከት ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህም የሚመጣው እንደ ጥላ መዘዋወር ወይም መለዋወጥ ከሌለበት ከብርሃን አባት ከእግዚአብሔር ነው።