መዝሙር 83:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንድነት በአንተ ላይ አሤሩ፤ በአንተ ላይ ለመነሣት የቃል ኪዳን ስምምነት አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንድ ሐሳብ ተስማምተው ተማከሩ፤ በአንተም ላይ ተማማሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፥ ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት፥ በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ብፁዕ ነው። |
በተለይም መርዶክዮስ አይሁዳዊ መሆኑን በተረዳ ጊዜ መርዶክዮስን ብቻ መግደል በቂ እንዳልሆነ ተገነዘበ፤ ስለዚህም በመላው የፋርስ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ግዛት ውስጥ ያሉትን የመርዶክዮስ ወገን የሆኑትን አይሁድን ሁሉ ለማጥፋት ዕቅድ አወጣ።
ሶርያ ከእስራኤል መንግሥት ጋር በመተባበር የጦር ቃል ኪዳን መግባትዋን የይሁዳ ንጉሥ በሰማ ጊዜ እርሱና ሕዝቡ ደንግጠው ልባቸው በነፋስ እንደ ተመታ ዛፍ ተናወጠ።
“እነዚህ ሕዝቦች፦ ‘እግዚአብሔር የመረጣቸውን እነዚያን ሁለት መንግሥታት ትቶአቸዋል’ ብለው ሕዝቤን በመናቅ በሕዝብነት እንደማያውቁአቸው አላስተዋልክምን?”
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ፍልስጥኤማውያን በማያቋርጥ ጠላትነት በቀልን ተበቅለዋል፤ ይህም የጥፋት በቀል ተንኰልን በተመላ ልብ ነበር።
ከነዓናውያንና ሌሎችም በዚህች ምድር የሚኖሩት ሁሉ ይህን ነገር ይሰማሉ፤ ስለዚህም ዙሪያችንን ከበው ሁላችንንም ይፈጁናል፤ ታዲያ ስለ ክብርህ የምታደርገው ምንድን ነው?”