ከሬሳውም የሚተርፈው እንደ ፍግ በዚያ ይበተናል፤ ስለዚህም ማንም እርስዋነትዋን ለይቶ በማወቅ፦ ይህች ኤልዛቤል ናት፥ ሊል አይችልም’ ያለው ነው።”
መዝሙር 83:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱን በዔንዶር ድል አደረግሃቸው፤ ሬሳቸውም በሜዳ ላይ በስብሶ ቀረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም በዓይንዶር ጠፉ፤ እንደ ምድርም ጕድፍ ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ምድያምና እንደ ሲሣራ፥ በቂሶንም ወንዝ እንደ ኢያቢስ አድርግባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፤ በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ። |
ከሬሳውም የሚተርፈው እንደ ፍግ በዚያ ይበተናል፤ ስለዚህም ማንም እርስዋነትዋን ለይቶ በማወቅ፦ ይህች ኤልዛቤል ናት፥ ሊል አይችልም’ ያለው ነው።”
ሁሉም በአሠቃቂ በሽታ ያልቃሉ፤ የሚያለቅስላቸውም ሆነ የሚቀብራቸው እንኳ አያገኙም፤ ሬሳቸው እንደ ጒድፍ በሜዳ ላይ ይከመራል፤ በጦርነትና በራብ ያልቃሉ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ምግብ ይሆናል።
ዐፅሞቻቸው ተሰብስበው በመቀበር ፈንታ፥ እንደ ጒድፍ የትም ይጣላሉ፤ እነርሱም፥ ሕዝቡ በማምለክና ምክር በመጠየቅ በፍቅር ያገለግሉአቸው በነበሩት በፀሐይ፥ በጨረቃና በከዋክብት ፊት ይበተናሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ኃጢአት በመሥራት እኔን ስለ በደሉ እንደ ዕውሮች እስኪደናበሩ ድረስ በሰዎች ላይ ታላቅ መከራ አመጣለሁ፤ ደማቸው እንደ ትቢያ ይፈስሳል፤ ሬሳቸውም እንደ ጒድፍ የትም ይጣላል።”
በይሳኮርና በአሴር ግዛት ውስጥ ምናሴ ቤትሼንና መንደሮችዋ፥ ይብልዓምና መንደሮችዋ፥ የዶር ኑዋሪዎችና መንደሮችዋ የዕንዶር ኑዋሪዎችና መንደሮችዋ፥ የታዕናክ ኑዋሪዎችና መንደሮችዋ፥ የመጊዶና ኑዋሪዎችና መንደሮችዋ፥ (በሦስተኛው ተራ ዶር የተባለው ናፋት ዶርም ይባላል)። እነዚህም ሁሉ የምናሴ ይዞታዎች ሆኑ።
ባራቅ ከሠራዊቱ ጋር አደጋ በጣለ ጊዜ እግዚአብሔር ሲሣራን ከሠረገሎቹና ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር በአደናጋሪ ሁከት ላይ እንዲወድቅ አደረገው፤ ሲሣራም ከሠረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ።
ባራቅም ሠረገሎቹንና ሠራዊቱን የአሕዛብ ይዞታ እስከ ሆነችው እስከ ሐሮሼት ድረስ አሳደዳቸው፤ የሲሣራም ሠራዊት በሙሉ በሰይፍ ተገደሉ፤ አንድ ሰው እንኳ አልተረፈም።
ዖሬብና ዘኤብ የተባሉ ሁለት የምድያማውያን መሪዎችንም ማረኩ፤ ዖሬብን “የዖሬብ አለት” ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ፥ ዘኤብንም “የዘኤብ የወይን መጭመቂያ” ተብሎ በሚጠራው ቦታ ገደሉአቸው፤ ከዚህም በኋላ የቀሩትን ምድያማውያን ማሳደድ ቀጠሉ፤ የዖሬብንና የዘኤብንም ራሶች ቈርጠው ወደ ጌዴዎን አመጡለት፤ በዚያን ጊዜ ጌዴዎን ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በኩል ነበረ።
ከዚህ በኋላ ሳኦል “ሙታን ጠሪ የሆነች አንዲት ሴት ፈልጉልኝ፤ እኔም ሄጄ ምክር እጠይቃታለሁ” ሲል ባለሟሎቹን አዘዘ። እነርሱም “አንዲት ዔንዶራዊት አለች” ሲሉ መለሱለት።