አምላክ ሆይ! እባክህ ዝም አትበል፤ አትተወን፤ ችላ አትበል!
አምላክ ሆይ፤ ዝም አትበል፤ አምላክ ሆይ፤ ጸጥ አትበል፤ ቸል አትበል።
የአሳፍ የምስጋና መዝሙር።
የኀያላን አምላክ ሆይ፥ ማደሪያዎችህ እጅግ የተወደዱ ናቸው።
መከታዬ እግዚአብሔር ሆይ! ወደ አንተ ስጣራ ጩኸቴን ስማ! አንተ ካልሰማኸኝ ግን ወደ መቃብር ከሚወርዱት እንደ አንዱ መሆኔ ነው።
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ይህን ተመልክተሃል፤ ስለዚህ ጌታ ሆይ! ዝም አትበል! ከእኔም አትራቅ!
ጌታ ሆይ! ንቃ! ስለምንስ ታንቀላፋለህ? ተነሥ! ለዘለዓለም አትተወን!
ኀያሉ እግዚአብሔር አምላክ ይናገራል፤ ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያዋ ድረስ፥ በምድር ያለውን ሰው ሁሉ ይጠራል።
አምላካችን ይመጣል፤ ዝም አይልም፤ የሚያቃጥል እሳት በፊቱ ነው፤ ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስም በዙሪያው ነው።
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለረጅም ጊዜ ታገሥኩ፤ ጸጥ ብዬም ራሴን ገታሁ፤ አሁን ግን ምጥ እንደ ያዛት ሴት ከፍተኛ ድምፅ አሰማለሁ፤ የቊጣ እስትንፋስ እተነፍሳለሁ።