መዝሙር 81:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እግዚአብሔር ጠላቶቹን በኀያል ሥልጣኔ ድል በነሣሁለት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባንበረከክኋቸው ነበር፤ እጄን በባላጋራዎቻቸው ላይ ባነሣሁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቤስ ሰምቶኝ ቢሆን፥ እስራኤልም በመንገዴ ሄደው ቢሆን፥ |
“ትእዛዞቼን በጥንቃቄ ሰምታችሁ ቢሆንማ ኖሮ፥ በረከታችሁ እንደማይደርቅ የወንዝ ውሃ፥ ጽድቃችሁም እንደ ባሕር ሞገድ በብዛት በመጣላችሁ ነበር!
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ሰይፍ ሆይ! ተባባሪዬ በሆነው በእረኛዬ ላይ ንቃ! በጎቹ ይበተኑ ዘንድ እረኛውን ምታ! እኔም በታናናሾቹ ላይ እጄን አነሣለሁ።
ስለዚህ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እዚያም የሚኖሩትን ሕዝቦች አትፍሩአቸው፤ እኛ በቀላሉ በጦርነት ድል እንነሣቸዋለን፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፎአል፤ ስለዚህ ፈጽሞ አትፍሩአቸው።”
“እንግዲህ እስራኤል ሆይ! እግዚአብሔር አምላክህን እንድትፈራው፥ በመንገዱ ሁሉ እንድትሄድ፥ እንድትወደው በሙሉ ልብህና በሙሉ ሐሳብህ እንድታመልከው፥ ለደኅንነትህ ሲባል እኔ ዛሬ የማዝህን የእግዚአብሔር አምላክህን ትእዛዝና ድንጋጌ እንድትጠብቅ ነው እንጂ እርሱ ሌላ ከአንተ ምን ይፈልጋል?
አምላካችሁ እግዚአብሔር እነዚህን ሕዝቦች ከፊታችሁ ማባረሩን እንደማይቀጥል በእርግጥ ዕወቁ፤ እንዲያውም አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከዚህች መልካም ምድር እስክትጠፉ ድረስ እነዚህን ሕዝቦች ለጀርባችሁ መግረፊያ፥ ለዐይኖቻችሁ እንደሚወጋ እሾኽ፥ እንዲሁም አደገኛ ወጥመድና መውደቂያ ጒድጓድ ይሆኑባችኋል።