ለሕዝቤ ለእስራኤል መኖሪያ አዘጋጅቴ በራሳቸው ቦታ እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤ ለእነርሱ መሳፍንትን ከሾምኩበት ጊዜ ጀምሮ ክፉ አድራጊዎች ቀድሞ ያደርጉት እንደ ነበረው አያስጨንቋቸውም፤ አንተንም ከጠላቶችህ ሁሉ አሳርፍሃለሁ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ከቤትህ አልጋህን የሚወርሱ ልጆች እተካልሃለሁ ብሎ ይገልጥልሃል።
መዝሙር 80:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምታድግበትን ቦታ መነጠርህላት፤ ሥሮችዋ በመሬት ውስጥ ጠልቀው መሠረት ያዙ፤ በምድሩም ላይ ተንሰራፋች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሬቱን መነጠርህላት፤ እርሷም ሥር ሰድዳ አገሩን ሞላች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግብጽ የወይን ግንድ አመጣህ፥ አሕዛብን አባረርህ እርሷንም ተከልህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተስ ብትሰማኝ የድንገት አምላክ አልሆንህም፥ ለሌላ አምላክም አትስገድ። |
ለሕዝቤ ለእስራኤል መኖሪያ አዘጋጅቴ በራሳቸው ቦታ እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤ ለእነርሱ መሳፍንትን ከሾምኩበት ጊዜ ጀምሮ ክፉ አድራጊዎች ቀድሞ ያደርጉት እንደ ነበረው አያስጨንቋቸውም፤ አንተንም ከጠላቶችህ ሁሉ አሳርፍሃለሁ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ከቤትህ አልጋህን የሚወርሱ ልጆች እተካልሃለሁ ብሎ ይገልጥልሃል።
በኖረበትም ዘመን ሁሉ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ መላው የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ያለስጋት በሰላም ይኖር ነበር፤ እያንዳንዱ ቤተሰብ የራሱ የሆነ የወይን ተክልና የበለስ ዛፍ ስለ ነበረው በእነዚህ ተክሎች ጥላ ሥር ያርፍ ነበር።
ለውትድርና አገልግሎት ብቁ የሆኑትን ሰዎች ጠቅላላ ድምር ለዳዊት አስታወቀ፤ እነርሱም ከእስራኤል አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ሲሆኑ፥ ከይሁዳ ደግሞ አራት መቶ ሰባ ሺህ ነበሩ፤
እነርሱ ምድርን የወረሱት በሰይፋቸው አይደለም፤ ድል አድርገው የወሰዱትም በራሳቸው ኀይል አይደለም፤ ይህን ሁሉ ያደረጉት አንተ ስለ ወደድካቸውና ከእነርሱም ጋር በመሆን በኀይልህና በብርታትህ ስለ ረዳሃቸው ነው።
መሬቱን በመቈፈርና ድንጋዩንም ለቅሞ በማውጣት ምርጥ የሆነውን የወይን ሐረግ ተከለበት፤ በመካከሉም መጠበቂያ የሚሆን ማማ ሠራለት፤ ጒድጓድ ቆፍሮም የወይን ፍሬ መጭመቂያ አበጀለት። ከዚያን በኋላ መልካም ፍሬ ያፈራል ብሎ ጠበቀ፤ ነገር ግን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ።
በሁለቱ አሞራውያን ነገሥታት ላይ እንዳደረግሁት አስቀድሜ ከፊታችሁ ያባረራቸውን ተርብ ሰደድኩባቸው፤ ይህ በእናንተ ሰይፍ ወይም በእናንተ ቀስት የሆነ አይደለም።