Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 80:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የወይን ሐረግን ከግብጽ አመጣህ፤ ሌሎች ሕዝቦችን አስወግደህ በምድራቸው እርስዋን ተከልክ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከግብጽ የወይን ግንድ አመጣህ፤ አሕዛብን አባርረህ እርሷን ተከልሃት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ መልሰን፥ ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሕዝቤ ሆይ፥ ስማኝ እነ​ግ​ር​ሃ​ለ​ሁም፤ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እመ​ሰ​ክ​ር​ል​ሃ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 80:8
16 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ! ወደ አንተ በምጣራበት ጊዜ አታሳፍረኝ፤ ክፉዎች ግን ይፈሩ፤ ጸጥ ብለውም ወደ ሲኦል ይውረዱ።


በቀድሞ ዘመን እጆችህ ያደረጉትን ድርጊት ሁሉ አባቶቻችን ነግረውናል፤ ይኸውም፥ እነርሱን ለመትከል ሕዝቦችን አባረሃል፤ እነርሱን ለማደላደል ነዋሪዎቹን አጥፍተሃል።


በሕዝብህ ላይ የችግር ቀን አመጣህ፤ እንድንንገዳገድ ያደረገንን የወይን ጠጅንም ሰጠኸን።


ከእነርሱ በፊት አሕዛብን አባረረ፤ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ ለእስራኤል ነገዶች አከፋፈለ፤ ቤቶቻቸውንም ለራሱ ሕዝብ ሰጠ።


ብዙ መሪዎች የወይን ተክል ቦታዬን አጥፍተዋል፤ የእርሻ ቦታዎቼንም ረጋግጠዋል፤ ደስ የምታሰኘውን ምድሬንም ወደ በረሓነት ለውጠዋታል።


እኔ ከተመረጠ ዘር መልካም የወይን ተክል አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን ተለውጠሽ እንደ ተበላሸ የበረሓ የወይን ተክል ሆነሻል።


ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በዱር ካሉ ዛፎች መካከል የወይንን ግንድ ለማገዶ እንዳደረግሁት የኢየሩሳሌምን ሕዝብ እንዲሁ አደርገዋለሁ።


ተክሉም አደገና ከምድር ብዙ ከፍ ሳይል በሰፊው የተንሰራፋ የወይን ተክል ሆነ፤ ቅርንጫፎቹ ወደ ንስሩ ከፍ ብለው አደጉ፤ ሥሮቹም ወደ መሬት ዘልቀው ገቡ፤ የወይን ተክሉ ብዙ ቅርንጫፎችና ቅጠሎች አብቅሎ ነበር።


እናትህ በውሃ አጠገብ እንደ ተተከለች የወይን ተክል ነበረች፤ እርስዋም ከውሃው መትረፍረፍ የተነሣ በቅርንጫፎችዋና በፍሬ እንደ ተሞላች የወይን ተክል ሆነች፤


እግዚአብሔር ከፊታቸው ያባረረላቸውን የአሕዛብን አገር በወረሱ ጊዜ አባቶቻችን ይህችን የተቀበሉአትን ድንኳን ከኢያሱ ጋር ወደዚያ አገቡአት፤ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ እዚያ ኖረች።


ከሊባኖስ እስከ ሚስረፎትማይም ድረስ በተራራማው አገር የሚኖሩ ነዋሪዎች፥ ማለት ሲዶናውያንን ሁሉ፥ እኔ ራሴ ከእስራኤላውያን ፊት አባርራቸዋለሁ፤ አንተ ግን እኔ እንዳዘዝኩህ ምድሪቱን ለእስራኤላውያን ርስት አድርገህ አከፋፍል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos