መዝሙር 78:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው ዐመፀኞችና እምቢተኞች አይሆኑም፤ እነዚያ እግዚአብሔርን በማመን የጸኑ አልነበሩም፤ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው አልኖሩም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እንደ አባቶቻቸው፣ እልኸኞችና ዐመፀኞች፣ ልቡን ያላቀና፣ መንፈሱም በእግዚአብሔር የማይታመን ትውልድ አይሆኑም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ አባቶቻቸው እንዳይሆኑ ዐመፀኛና የሚያስመርር ትውልድ፥ ልቡን ያላቀና ትውልድ፥ መንፈሱም በእግዚአብሔር ዘንድ ያልታመነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀደመውን በደላችንን አታስብብን፥ አቤቱ፥ ምሕረትህ በቶሎ ያግኘን፥ እጅግ ተቸግረናልና። |
ይህም ሁሉ ሆኖ አንዳንድ መልካም ነገር አድርገሃል፤ ይኸውም ሕዝቡ ያመልካት የነበረችውን አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስሎችን ሁሉ ከምድሪቱ አስወግደሃል፤ የእግዚአብሔርንም ፈቃድ ለይተህ ለመፈጸም ጥረት አድርገሃል።”
ነገር ግን በከፍተኛ ቦታዎች ላይ የሚገኙትን የማምለኪያ ቦታዎች አላስወገደም፤ ሕዝቡም ወደ ቀድሞ አባቶቹ አምላክ ወደ እግዚአብሔር በሙሉ ልቡ ገና አልተመለሰም ነበር።
“የቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን በሥርዓት ያላነጹ ቢሆኑም እንኳ እነሆ በፍጹም ልባቸው አንተን በማምለክ ላይ ይገኛሉ፤ ስለዚህ በቸርነትህ ይቅር በላቸው!” ሲል ጸለየ፤
ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ታማኞች እንዳልሆኑት እንደ ቀድሞ አባቶቻችሁና እንደ ወገኖቻችሁ እስራኤላውያን አትሁኑ፤ እንደምታውቁት እግዚአብሔር እነርሱን ለጥፋት አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል፤
የቀድሞ አባቶቻችን በግብጽ ምድር እርሱ ያደረገውን ድንቅ ነገር ሁሉ አላስተዋሉም፤ ብዙዎቹን የቸርነት ሥራዎቹን አላስታወሱም፤ በቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁ።
መጠጊያ ላጡ ብቸኞች የሚኖሩበትን ቤት ይሰጣቸዋል፤ እስረኞች ነጻ ወጥተው በብልጽግና እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፤ ዐመፀኞች ግን በሚያቃጥል በረሓ ይኖራሉ።
የምትሄዱት በማርና በወተት ወደበለጸገች ለም ምድር ነው፤ ነገር ግን እናንተ እልኸኞች ስለ ሆናችሁ በመንገድ እንዳላጠፋችሁ አብሬአችሁ አልሄድም።”
እግዚአብሔርም ለሕዝቡ እንዲህ ብሎ እንዲነግረው ሙሴን አዞት ነበር፦ “እናንተ እልኸኞች ስለ ሆናችሁ ለአንድ አፍታ እንኳ አብሬአችሁ ብሄድ ፈጽሞ እደመስሳችኋለሁ፤ አሁንም ጌጣጌጦቻችሁን አስወግዱ፤ ስለ እናንተ የማደርገውንም እወስናለሁ።”
እንዲህም አለ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ በአንተ ዘንድ ሞገስን አግኝቼ ከሆነ ከእኛ ጋር አብረህ እንድትወጣ እለምንሃለሁ፤ ይህ ሕዝብ እልኸኛ ነው፤ ነገር ግን ኃጢአታችንንና ክፉ ሥራችንን ሁሉ ይቅር በል፤ የራስህ ሕዝብ አድርገህ ተቀበለን።”
ለልጆቻቸውም እንዲህ ብዬ ነገርኳቸው፦ “የቀድሞ አባቶቻችሁ ባወጡት ድንጋጌ አትመሩ፤ ሥርዓታቸውንም አትከተሉ፤ ወይም በጣዖቶቻቸው አትርከሱ፤
ነገር ግን እነርሱ ዐመፀኞች ሆኑ እንጂ እኔን ለማዳመጥ ፈቃደኞች አልሆኑም፤ ዐይኖቻቸው ያተኰሩባቸውን አጸያፊ ምስሎች አላስወገዱም፤ የግብጽንም ጣዖት ማምለክ አልተዉም፤ ስለዚህ በግብጽ በነበሩበት ጊዜ ቊጣዬን ላወርድባቸው አስቤ ነበር።
እርሱም ሄዶ እግዚአብሔር ጸጋውን ለሕዝቡ እንዴት እንደ ሰጠ ባየ ጊዜ ደስ አለው፤ ሁሉም በሙሉ ልብ ጸንተው ለጌታ ታማኞች ሆነው እንዲኖሩም መከራቸው።
የእስራኤል ሕዝብ ምን ያኽል ዐመፀኞችና አንገተ ደንዳኖች እንደ ሆኑ ዐውቃለሁ፤ በእኔ ሕይወት ዘመን ከእነርሱ ጋር ሳለሁ እንኳ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፁ ናቸው፤ ከሞትሁ በኋላማ ከዚህ ይበልጥ ያምፃሉ፤
እኔ እነርሱን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ፊታቸውን መልሰው ከእኔ በመራቅ ባዕዳን አማልክትን ሲያመልኩ ኖረዋል፤ እንግዲህ በእኔ ላይ ሲያደርጉት የነበረውን ሁሉ እነሆ በአንተም ላይ መፈጸም ጀምረዋል፤