መዝሙር 77:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እረኛ የበጎችን መንጋ እንደሚመራ፥ አንተም በሙሴና በአሮን አማካይነት ሕዝብህን መራህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሙሴና በአሮን እጅ፣ ሕዝብህን እንደ በግ መንጋ መራኸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው፥ ያለፍከውም ኃይለኛ ውኆች በኩል ነው፤ ዱካህ ግን አልታወቀም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዓለቱን ይመታ ዘንድ ውኃንም ያፈስ ዘንድ ይችላልን? እንጀራን መስጠትና ለሕዝቡስ ማዕድን መሥራት ይችላልን?” |
የእስራኤል እረኛ፥ የዮሴፍን ልጆች እንደ መንጋ የምትመራ አምላክ ሆይ! በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋንህ ተቀምጠህ፥ ጸሎታችንን አድምጥ፤ ብርሃንህም ይብራ።
የእስራኤልን ሠራዊት ፊት ፊት ይመራ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ ኋላ ተመልሶ ደጀን ሆነ፤ የደመናውም ዐምድ አልፎ በኋላ በኩል ቆመ፤
ሁለት ቀንም ይሁን አንድ ወር፥ አንድ ዓመትም ይሁን ከዚያ የረዘመ ጊዜ ደመናው በድንኳኑ ላይ እስካረፈበት ጊዜ ድረስ አይንቀሳቀሱም ነበር፤ ደመናው ሲነሣ ግን ጒዞአቸውን ይቀጥሉ ነበር።