መዝሙር 77:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ያከናወንካቸውን ታላላቅ ሥራዎች አስታውሳለሁ፤ ባለፉት ዘመናት ያደረግኻቸው ተአምራት ትዝ ይሉኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርን ሥራ አስታውሳለሁ፤ የጥንት ታምራትህን በርግጥ አስታውሳለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ድካሜ ነው አልሁ፥ የልዑል ቀኝ መለወጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ረድኤቱንና ያሳያቸውን ተአምራቱን ረሱ፥ |
አገልጋዮቹ የሆናችሁ የእስራኤል ልጆች ሆይ! የእግዚአብሔር ምርጥ የሆናችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ! እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ድንቅ ነገሮች፥ የሰጠውን ፍርድና ያደረጋቸውን ተአምራት አስታውሱ።
አገልጋዮች የሆናችሁ የእስራኤል ልጆች ሆይ! የእግዚአብሔር ምርጥ የሆናችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ! እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ድንቅ ነገሮች፥ የሰጠውን ፍርድና ያደረጋቸውን ተአምራት አስታውሱ።
“አምላክ ሆይ፥ ከአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅድስናስ እንደ አንተ ያለ ባለግርማ ማን ነው? አንተ ያደረግሃቸውን ተአምራትና አስገራሚ ሥራዎች ሊያደርግ የሚችልስ ማን አለ?