በደጃፎቻችሁ መቃኖች ላይ የሚታየው ደም እናንተ የምትኖሩባቸውን ቤቶች ለይቶ የሚያሳይ ምልክት ይሆናል፤ እኔም ደሙን በማይበት ጊዜ አልፌአችሁ እሄዳለሁ፤ በዚህም ዐይነት ግብጻውያንን በመቅሠፍት በምመታበት ጊዜ፥ በእናንተ ላይ ምንም ዐይነት መቅሠፍት አይደርስባችሁም።
መዝሙር 74:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእንግዲህ ወዲህ ተአምራት አይኖሩም፤ ነቢያትም አይኖሩም፤ ይህ ሁኔታ እስከ መቼ እንደሚቈይ ከእኛ መካከል ማን ያውቃል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምናየው ምልክት የለም፤ ከእንግዲህ የሚነሣ አንድም ነቢይ የለም፤ ይህ እስከ መቼ እንደሚቀጥል የሚያውቅ በእኛ ዘንድ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምልክታችንን አናይም ከእንግዲህ ወዲህም ነቢይ አይኖርም፥ ይህም እስከ መቼ እንደሚቆይ የሚያውቅ በኛ ዘንድ የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን ለዘለዓለም ደስ ይለኛል፥ ለያዕቆብም አምላክ እዘምራለሁ፥ |
በደጃፎቻችሁ መቃኖች ላይ የሚታየው ደም እናንተ የምትኖሩባቸውን ቤቶች ለይቶ የሚያሳይ ምልክት ይሆናል፤ እኔም ደሙን በማይበት ጊዜ አልፌአችሁ እሄዳለሁ፤ በዚህም ዐይነት ግብጻውያንን በመቅሠፍት በምመታበት ጊዜ፥ በእናንተ ላይ ምንም ዐይነት መቅሠፍት አይደርስባችሁም።
የቅጽር በሮች ከመሬት በታች ተቀበሩ፤ መወርወሪያዎቻቸውም ተሰባብረው ወደቁ፤ ንጉሡና መሳፍንቱ አሁን በአሕዛብ መካከል በስደት ላይ ናቸው፤ የኦሪት ሕግ ትምህርት ከእንግዲህ ወዲህ አይሰጥም፤ ነቢያትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ራእይ አይገለጥላቸውም።
አንዱ መቅሠፍት ሌላውን ያስከትላል፤ አንዱ ወሬም ሌላውን ወሬ ተከታትሎ ይመጣል፤ ነቢያት ያዩትን ራእይ እንዲነግሩአችሁ ትለምኑአቸዋላችሁ፤ ካህናት ሕዝቡን የሚያስተምሩት ሕግ፥ ሽማግሌዎችም ለሕዝቡ የሚሰጡት ምክር ጠፋባቸው።
“እነሆ በምድር ላይ ራብን የማመጣበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜም ሰዎች የሚራቡትና የሚጠሙት የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ነው እንጂ ምግብና ውሃ በማጣት አይደለም፤ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
‘ራእይ እናያለን፥ ትንቢት እንናገራለን’ የሚሉ ሁሉ ስለማይሳካላቸው ይዋረዳሉ፤ እግዚአብሔርም መልስ ስለማይሰጣቸው ከማፈራቸው የተነሣ ፊታቸውን በእጃቸው ሸፍነው ይሄዳሉ።”
እግዚአብሔርም ደግሞ ምልክቶችን፥ ድንቅ ነገሮችን፥ ልዩ ልዩ ተአምራትን በማድረግና እንደ ፈቃዱ በታደሉት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አማካይነት ምስክርነታቸውን አጽንቶአል።
ወጣቱ ሳሙኤል በዔሊ የአመራር ሥልጣን ሥር ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ዘወትር አይሰማም ነበር፤ ራእይም አይታይም ነበር።