መዝሙር 74:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቶችህ ዘወትር የሚጮኹትን ጩኸትና የሚደነፉትን ድንፋታ አስታውስ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባላጋራዎችህን ድንፋታ፣ ዘወትር የሚነሣውን የጠላቶችህን ፉከራ አትርሳ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጠላቶችህን ቃል አትርሳ፥ የተቃዋሚዎችህ ድንፋታ ሳያቋርጥ ወደ አንተ ይወጣል። |
በእኔ ላይ ስለ መቈጣትህና ስለ ልብህ ትዕቢት ሁሉ ሰምቼአለሁ፤ ስለዚህ አሁን በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህም ልጓም አግብቼ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”
ጠላቶቻችሁ ሁሉ በእናንተ ላይ አፋቸውን ይከፍታሉ፤ ያሽሟጥጣሉ ጥርሳቸውን ያፋጫሉ፤ እንዲህ ሲሉም ይጮኻሉ፦ “ደመሰስናቸው! እሰይ ይህ የምንመኘው ቀን ነበር! በመጨረሻም አየነው።”
“ተነሥተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ እኔ የሕዝብዋን ክፋት ተመልክቼአለሁ። ድምፅህንም ከፍ አድርገህ እርስዋን በመገሠጽ ተናገር።”
እነርሱ በበጉ ላይ ጦርነት ይከፍታሉ፤ ነገር ግን በጉ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ ድል ይነሣቸዋል፤ ከእርሱ ጋር ያሉት የተጠሩ የተመረጡና የታመኑ ናቸው።”