የአሦር ንጉሠ ነገሥት ሕያው እግዚአብሔርን እንዲሰድብለት ከፍተኛ ባለሥልጣኑን ልኮአል፤ አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ስድብ ሰምቶ ተሳዳቢውን ይቀጣ ይሆናል፤ ስለዚህ ከሕዝባችን መካከል በሕይወት ለተረፉት ሰዎች እባክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ።”
መዝሙር 74:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ፥ ጠላቶችህ በአንተ ላይ እንደሚሳለቁ ተመልከት፤ እነርሱ ሞኞች ስለ ሆኑ ስምህን ይዳፈራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላት እንዴት እንደሚያሾፍ፣ ሞኝ ሕዝብም ስምህን እንዴት እንዳቃለለ ዐስብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንንም አስታውስ፥ ጠላት በጌታ ተሳለቀ፥ አላዋቂ ሕዝብም በስምህ ቀለደ። |
የአሦር ንጉሠ ነገሥት ሕያው እግዚአብሔርን እንዲሰድብለት ከፍተኛ ባለሥልጣኑን ልኮአል፤ አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ስድብ ሰምቶ ተሳዳቢውን ይቀጣ ይሆናል፤ ስለዚህ ከሕዝባችን መካከል በሕይወት ለተረፉት ሰዎች እባክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ።”
እግዚአብሔር ሆይ! ኢየሩሳሌም በተያዘችበት ቀን ኤዶማውያን ያደረጉትን አስብ፤ “እስከ መሠረትዋ አፈራርሳችሁ ጣሉአት!” እያሉ መጮኻቸውንም አስታውስ።
እናንተ ሞኞችና ኅሊና ቢሶች፥ የእግዚአብሔርን ዋጋ የምትከፍሉ በዚህ ዐይነት ነውን? እርሱ የፈጠራችሁ አባታችሁ አይደለምን? የመሠረታችሁስ እርሱ አይደለምን?
ታላቂቱ ከተማ ከሦስት ተከፈለች፤ የአሕዛብ ከተሞችም ፈራረሱ፤ እግዚአብሔር ታላቂቱን ባቢሎንን አስታወሰ፤ የብርቱ ቊጣው ወይን ጠጅ የተሞላበትን ጽዋ እንድትጠጣም አደረጋት።