ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ እባቡን እንዲህ አለው፦ “ይህን በማድረግህ ከእንስሶችና ከአራዊት ሁሉ ተለይተህ የተረገምክ ሁን፤ ከዛሬ ጀምሮ በደረትህ እየተሳብክ ሂድ፤ ዕድሜህን ሙሉ ዐፈር ብላ፤
መዝሙር 72:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምድረ በዳ የሚኖሩ በፊቱ ይስገዱ፤ ጠላቶቹም ወደ መሬት ወድቀው ትቢያ ይላሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የበረሓ ዘላኖች በፊቱ ይሰግዳሉ፤ ጠላቶቹም ዐፈር ይልሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፊቱም የኢትዮጵያ ሰዎች ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አፋቸውንም በሰማይ አኖሩ፥ አንደበታቸውም በምድር ላይ ተመላለሰ። |
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ እባቡን እንዲህ አለው፦ “ይህን በማድረግህ ከእንስሶችና ከአራዊት ሁሉ ተለይተህ የተረገምክ ሁን፤ ከዛሬ ጀምሮ በደረትህ እየተሳብክ ሂድ፤ ዕድሜህን ሙሉ ዐፈር ብላ፤
ነገሥታት አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል። የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቂአለሽ፤ የእኔን ርዳታ ለማግኘት የሚጠባበቁ ከቶ አያፍሩም።”
እንደ እባብና እንደ ሌሎችም ተንፏቃቂ ፍጥረቶች ትቢያ ይልሳሉ፤ ከምሽጎቻቸው ወጥተው እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ፤ በፍርሃትም ወደ አንተ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ፤ አንተንም እየፈሩ ይኖራሉ።