መዝሙር 72:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክቡር ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን! ክብሩ በምድር ሁሉ ይሙላ! አሜን! አሜን! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክቡር ስሙ ለዘላለም ይባረክ፤ ምድርም ሁሉ በክብሩ ትሞላ። አሜን፤ አሜን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምስጋናው ስም ለዓለምና ለዘለዓለም ይባረክ፥ ምስጋናውም ምድርን ሁሉ ይምላ። አሜን፥ አሜን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ፥ ስለ ኀጢአታቸውም ጠፉ። |
ኢያሱ፥ ቃድሚኤል፥ ባኒ፥ ሐሸባንያ፥ ሼሬብያ፥ ሆዲያ፥ ሸባንያና ፐታሕያ ተብለው የሚጠሩት ሌዋውያን፦ “ተነሥታችሁ በመቆም ዘለዓለማዊውን አምላካችሁን እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ከምስጋናና ከበረከት ሁሉ በላይ፥ ከፍ ከፍ ይበል! በሉ” አሉአቸው።
በእግዚአብሔር ቅዱስ ተራራ ላይ ምንም ጒዳት አይደርስም፤ ባሕር በውሃ እንደሚሞላ ምድርም እግዚአብሔርን በሚያውቁና በሚያከብሩ ሰዎች ትሞላለች።
“አሜን! እግዚአብሔር እንዳልከው ያድርግ! የቤተ መቅደሱን ዕቃዎች በማምጣትና የተማረኩትን ምርኮኞች በመመለስ እግዚአብሔር አንተ የተናገርከውን ትንቢት ይፈጽም።
እነሆ፥ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ዳር እስከ ዳር ለእኔ ክብር ይሰጣሉ፤ በየትኛውም ስፍራ ለእኔ ዕጣን እያጠኑ ንጹሕ መሥዋዕት ያቀርቡልኛል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ያከብሩኛል።
ይህም ውሃ ወደ ሰውነትሽ ገብቶ ሆድሽን ያሳብጠው፤ ማሕፀንሽንም ያኰማትረው።’ ሴትዮዋም ‘አሜን፥ እግዚአብሔር እንዲሁ ያድርግብኝ’ ብላ ትመልሳለች።
በሰማይና በምድር፥ ከምድር በታችና በባሕር፥ በውስጣቸውም ፍጥረቶች ሁሉ “በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ለበጉም ምስጋና፥ ገናናነት፥ ክብርና ኀይል ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን!” ሲሉ ሰማሁ።