Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ራእይ 22:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 የእነዚህ ነገሮች ምስክር የሆነው “በእርግጥ፥ በቶሎ እመጣለሁ!” ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እነዚህን ነገሮች የሚመሰክረው፣ “አዎ፣ ቶሎ እመጣለሁ” ይላል። አሜን፤ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፤ ና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ይህን የሚመሰክር “አዎን በቶሎ እመጣለሁ፤” ይላል። አሜን፤ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ይህን የሚመሰክር “አዎን በቶሎ እመጣለሁ፤” ይላል። አሜን፤ ጌታ ኢየሱስ ሆይ!ጅ ና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ይህን የሚመሰክር፦ አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 22:20
15 Referencias Cruzadas  

ውዴ ሆይ! ፈጥነህ ወደ እኔ ና፤ የቅመም ተክሎች በሚበቅሉባቸው ተራራዎች ላይ የሚዘል አጋዘን ወይም የዋልያ ግልገል ምሰል።


ይህም በሚፈጸምበት ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ “እነሆ፥ እርሱ አምላካችን ነው፤ በእርሱ ስለ ታመንን አድኖናል፤ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ እኛም በእርሱ ታምነናል፤ እርሱ ስለ ታደገን በደስታ ተሞልተን ሐሴት እናደርጋለን!” ይላሉ።


ኢየሱስ ያደረጋቸው ሌሎች ብዙ ነገሮች ደግሞ አሉ። እኔ እንደሚመስለኝ እርሱ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ አንድ በአንድ ቢጻፉ ኖሮ የሚጻፉትን መጻሕፍት ዓለም ራሱ መሸከም ባልቻለም ነበር።


ጌታን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን! ጌታችን ሆይ፥ ና!


ከእንግዲህ ወዲህ የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤ ይህንንም አክሊል ያ ትክክለኛ ፍርድን ፈራጁ ጌታ በዚያን ቀን ይሰጠኛል፤ የሚሰጠውም ለእኔ ብቻ ሳይሆን የእርሱን መገለጥ ለሚወድዱ ሁሉ ነው።


ለዚህም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፤ “ያ የሚመጣው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ይመጣል፤ አይዘገይምም፤


እንዲሁም ክርስቶስ የብዙዎችን ኃጢአት ለማስወገድ አንድ ጊዜ ተሠውቶአል፤ ደግሞም ኃጢአትን ለመሸከም ሳይሆን እርሱን የሚጠባበቁትን ለማዳን ሁለተኛ ጊዜ ይገለጣል።


እኔም ሕያው ነኝ፤ ሞቼ ነበር፤ ነገር ግን እነሆ፥ ለዘለዓለም ሕያው ነኝ፤ በሞትና በሲኦል ላይ ሥልጣን አለኝ።


ዮሐንስም ስለ እግዚአብሔር ቃልና ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ አስተማረው እውነት፥ እንዲሁም ስላየውም ነገር ሁሉ መሰከረ።


ስለዚህ ንስሓ ግባ፤ አለበለዚያ በቶሎ ወደ አንተ መጥቼ እንደ ሰይፍ ባለው ከአፌ በሚወጣው ቃል እዋጋቸዋለሁ።


ቀጥሎም እንዲህ አለኝ፤ “ጊዜው የቀረበ ስለ ሆነ የዚህን መጽሐፍ የትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው፤


“እነሆ! እኔ በቶሎ እመጣለሁ! ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው የምሰጠውን ዋጋ ይዤአለሁ፤


እነሆ፥ በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል የሚሰማውን ሁሉ አስጠነቅቃለሁ፤ ማንም በዚህ ቃል ላይ አንዳች ነገር ቢጨምር፥ በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች እግዚአብሔር ይጨምርበታል።


ኢየሱስም “እነሆ! እኔ በቶሎ እመጣለሁ! የዚህን መጽሐፍ የትንቢት ቃል የሚጠብቅ የተመሰገነ ነው!” አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos