አምላክ ሆይ! ሞኝነቴን አንተ ታውቃለህ፤ ኃጢአቴ ከአንተ የተሰወረ አይደለም።
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ቂልነቴን ታውቃለህ፤ በደሌም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።
በከንቱ የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጉር በዙ፥ በዓመፅ ያሚያሳድዱኝ ጠላቶቼ በረቱ፥ በዚያን ጊዜ ያልቀማሁትን መለስሁ።
እኔ ድሃና ምስኪን ነኝ፤ እግዚአብሔርም ይረዳኛል፤ ረዳቴ መጠጊያዬም አንተ ነህ፥ አቤቱ አምላኬ አትዘግይ።
ልቤን ብትመረምር፥ በሌሊት ብትጐበኘኝ፥ ብትፈትነኝም፥ ከእኔ ክፋትን አታገኝም፤ አንደበቴም አይስትም።
የራሱን ስሕተት የሚያይ ማንም የለም፤ አምላኬ ሆይ! ከተሰወረ በደል አንጻኝ።
ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ ጠላቶቼ በእኔ ምክንያት እንዲደሰቱ አታድርግ፤ በኋላዬ ሆነው እንዲጠቃቀሱብኝም አታድርግ።
በሞኝነት ካደረግሁት ስሕተት የተነሣ ቊስሌ በስብሶ ይሸታል።
ጌታ ሆይ! የልቤን ፍላጎት ሁሉ ታውቃለህ፤ የእኔም መቃተት ለአንተ ምሥጢር አይደለም።
የሚያደርጉትን ሁሉ አያለሁ፤ ከእኔ የሚሰወር ምንም ነገር የለም፤ ኃጢአታቸው ሁሉ በፊቴ የተገለጠ ነው።