ትሑታን ይህን ባዩ ጊዜ ደስ ይላቸዋል፤ በጸሎት እግዚአብሔርን የምትሹ በርቱ።
ድኾች ይህን ያያሉ፤ ደስም ይላቸዋል፤ እናንተ እግዚአብሔርን የምትሹ ልባችሁ ይለምልም!
ቀንድና ሰኰና ካበቀለ ኰርማ ወይም ወይፈን ይልቅ ጌታን ደስ ያሰኘዋል።
ድኾች እስኪጠግቡ ይበላሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹት ያመሰግኑታል፤ ልባቸው በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ይደሰታል።
ጌታ ሆይ! የተትረፈረፈ ሀብት ያላቸው ሁሉ ይሰግዱልሃል። ለሞትና ለመቃብር የተቃረቡትም መጥተው ይንበረከኩልሃል።
ትሑቶችንም በትክክለኛው መንገድ ይመራቸዋል፤ መንገዱንም ያስተምራቸዋል።
በሙሉ ልቤ በእግዚአብሔር እመካለሁ፤ ትሑቶች ይህን ሰምተው ደስ ይበላቸው!
የኰርማዎችን ሥጋ እበላለሁን? ወይስ የፍየሎችን ደም እጠጣለሁን?
የምስጋና መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርብ፤ ስእለትህንም ለልዑል ስጥ።
እንዲሁም እናንተ አሁን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን እኔ እንደገና አያችኋለሁ፤ ልባችሁም ደስ ይለዋል፤ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም።
ይህንንም ብሎ እጆቹንና ጐኑን አሳያቸው፤ ደቀ መዛሙርቱም ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው።