La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 63:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በመቅደስህ ውስጥ አንተን ተመለከትኩ፤ ኀይልህንና ክብርህንም አየሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ በመቅደስ ውስጥ አየሁህ፤ ኀይልህንና ክብርህንም ተመለከትሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፥ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች በደረቅ መሬት፥ ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከክ​ፉ​ዎች ሴራ ከብ​ዙ​ዎች ዐመፅ አድ​ራ​ጊ​ዎች ሰው​ረኝ።

Ver Capítulo



መዝሙር 63:2
19 Referencias Cruzadas  

በእግዚአብሔርና በኀያል ሥልጣኑ ተማመኑ፤ ዘወትርም እርሱን ፈልጉ፤


በእግዚአብሔርና በኀያል ሥልጣኑ ተማመኑ፤ ዘወትርም እርሱን ፈልጉ።


በመቅደሱ እጆቻችሁን ለጸሎት ዘርግታችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑ!


ስለ ንጉሥነትህ ክብር ያወራሉ፤ ስለ ኀይልህም ይናገራሉ።


እግዚአብሔርን አንድ ነገር እለምነዋለሁ፤ የምለምነውም፦ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ የእግዚአብሔርን አስደናቂነት እንድመለከትና በቤተ መቅደሱም መጸለይ እንድችል ነው።


ቀንና ሌሊት ስለ ማልቅስ እንባዬ እንደ ምግብ ሆኖኛል፤ ጠላቶቼ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ ዘወትር ይጠይቁኛል።


አምላክ ሆይ! ከዚያም በኋላ ለአንተ ለምታስደስተኝ ወደ መሠዊያህ ሄጄ እሰግድልሃለሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ በገናዬን እየደረደርኩ አመሰግንሃለሁ።


አንተ በኃጢአት የምትደሰት አምላክ አይደለህም፤ ክፉዎችም ከአንተ ጋር አይኖሩም።


አምላክ ሆይ! የድል አድራጊነትህ ሰልፍ በሁሉም ይታያል፤ የእኔ ንጉሥና አምላክ በክብር አጀብ ወደ መቅደሱ ሲገባ ይታያል።


የኀይሉና የክብሩ መታወቂያ ምልክት የነበረችውን የቃል ኪዳን ታቦት፥ ጠላቶች ማርከው እንዲወስዱአት አደረገ።


በዙሪያው ያለው ክብርና ግርማ ነው፤ ኀይልና ውበትም በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።


ቤተ መቅደሴ ያረፈበትን ቦታ ለማስዋብ የሊባኖስ ግርማ የሆኑት ዝግባ አስታና ጥድ ወደ አንቺ እንዲመጡ ይደረጋሉ፤ እኔም የእግሬ ማረፊያ የሆነውን አከብረዋለሁ።


ካህናቱን በምድሪቱ በረከት አጠግባቸዋለሁ፤ ለሕዝቤም ቸርነቴን አትረፈርፍላቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”