መዝሙር 60:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጠላት መሣሪያ ማምለጥ እንዲችሉ፥ የሚፈሩህ አይተው የሚጠነቀቁበትን ምልክት ሰጠሃቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ከቀስት እንዲያመልጡ፣ ለሚፈሩህ ምልክት አቆምህላቸው። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድርን አናወጥሃት አወክሃትም፥ ተናውጣለችና ቁስልዋን ፈውስ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በድንኳንህ ለዘለዓለም እኖራለሁ፤ በክንፎችህ ጥላም እጋረዳለሁ፤ |
በዚያን ጊዜ ጌታ በመላው ዓለም ተበታትነው ይኖሩ የነበሩትን የእስራኤልንና የይሁዳን ሕዝብ ከአራቱ ማእዘን ሰብስቦ ያመጣቸው መሆኑን ለመንግሥታት ሁሉ የሚያሳውቅበትን አርማ ከፍ አድርጎ ያቆማል።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወንዶች ልጆችሽን በክንዳቸው፥ ሴቶች ልጆችሽንም በትከሻቸው ተሸክመው ያመጡ ዘንድ ለመንግሥታት ምልክት እሰጣለሁ፤ ለሕዝቦችም ዐርማን አነሣለሁ።