Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 59:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እርሱ በኀይለኛ ነፋስ እየተነዳ እንደሚመጣ ጐርፍ ስለ ሆነ በምዕራብ ያሉ ሕዝቦች የእግዚአብሔርን ስም በምሥራቅ ያሉት ክብሩን ይፈራሉ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 በምዕራብ ያሉት የእግዚአብሔርን ስም ይፈራሉ፤ በፀሓይ መውጫ ያሉት ለክብሩ ይገዛሉ፤ የእግዚአብሔር እስትንፋስ እንደ ተቋተ፣ እንደ ተከማቸም ጐርፍ ይመጣልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እርሱ የጌታ ነፋስ እንደሚነዳው እንደ ጐርፍ ፈሳሽ ይመጣልና በምዕራብ ያሉት የጌታን ስም፥ በፀሐይ መውጫም ያሉት ክብሩን ይፈራሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በም​ዕ​ራብ ያሉት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም፥ በፀ​ሐይ መው​ጫም ያሉት ክብ​ሩን ይፈ​ራሉ። መቅ​ሠ​ፍ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እንደ ኀይ​ለኛ ፈሳሽ በቍጣ ይመ​ጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እርሱ የእግዚአብሔር ነፋስ እንደሚነዳው እንደ ጐርፍ ፈሳሽ ይመጣልና በምዕራብ ያሉት የእግዚአብሔርን ስም፥ በፀሐይ መውጫም ያሉት ክብሩን ይፈራሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 59:19
25 Referencias Cruzadas  

ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያዋ ድረስ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን!


እስከ ምድር ዳርቻ ያሉ ሰዎች ሁሉ አስታውሰው ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ፤ በዓለም የሚገኙት ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ።


አምላክ ሆይ! ስእለቴን ሰማህ፤ አንተን ለሚፈሩ ሰዎች ያዘጋጀኸውን በረከት ለእኔም ሰጠኸኝ።


እነሆ፥ የእግዚአብሔር ኀይልና ግርማ ከሩቅ ይታያል፤ ነበልባልና ጢስ የቊጣው ምልክቶች ናቸው፤ በሚናገርበትም ጊዜ ቃሉ እንደ እሳት ይነዳል።


እስትንፋሱ እስከ አፍ ጢሙ ድረስ እንደ ሞላ ኀይለኛ የወንዝ ጐርፍ ነው። ሕዝቦችን በወንፊት እንደሚበጠር ብጣሪ አበጥሮ ያጠፋቸዋል። በመንጋጋቸውም ውስጥ የጥፋት ልጓም ለጒሞ ያጠፋቸዋል።


ይህንንም የማደርገው መላው ዓለም እኔ ብቻ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩና ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ያውቅ ዘንድ ነው።


ሕዝቦቼ ከሩቅ አገሮች ይመጣሉ፤ ከሰሜንና ከምዕራብ እንዲሁም ከሲኒም።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሀብትዋን እንደ ወንዝ ውሃ አበዛዋለሁ፤ የሕዝቦችንም ሀብት እንደ ወንዝ ጅረት አደርገዋለሁ፤ በክንድዋም ተይዛችሁ ትጠባላችሁ፤ በጭንዋም ላይ አድርጋ ትንከባከባችኋለች።


አሁን እኔ የአሦርን ንጉሥ ከኀይለኛ ሠራዊቱ ጋር በእነርሱ ላይ አስነሣዋለሁ፤ የሠራዊቱም አመጣጥ የኤፍራጥስን ወንዝ ሞልቶ እንደሚያጥለቀልቅ ማዕበል ይሆናል።


ከሰማይ ሁሉ በታች በምድር ላይ ያለ የመንግሥት ሥልጣን፥ ኀይልና ገናናነት ሁሉ ለልዑል እግዚአብሔር ቅዱሳን ይሰጣል፤ መንግሥታዊ ሥልጣናቸውም ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤ የዓለም ግዛቶች ሁሉም ለእነርሱ በመታዘዝ ያገለግሉአቸዋል።’ ”


እንደ እባብና እንደ ሌሎችም ተንፏቃቂ ፍጥረቶች ትቢያ ይልሳሉ፤ ከምሽጎቻቸው ወጥተው እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ፤ በፍርሃትም ወደ አንተ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ፤ አንተንም እየፈሩ ይኖራሉ።


ለዘሩባቤል እንዳስታወቀው መልአኩ የነገረኝ የሠራዊት አምላክ ቃል ይህ ነው፤ “ድል የምትነሣው በመንፈሴ እንጂ በኀይልና በብርታት አይደለም።


እነሆ፥ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ዳር እስከ ዳር ለእኔ ክብር ይሰጣሉ፤ በየትኛውም ስፍራ ለእኔ ዕጣን እያጠኑ ንጹሕ መሥዋዕት ያቀርቡልኛል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ያከብሩኛል።


ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ፤ ከአብርሃም፥ ከይስሐቅ፥ ከያዕቆብ ጋር በመንግሥተ ሰማይ በማዕድ ይቀመጣሉ እላችኋለሁ።


ከዚህ በኋላ ጌታ ኢየሱስ በአፉ እስትንፋስ የሚያጠፋውና በግርማ መምጣቱ የሚደመስሰው የዐመፅ ሰው ይገለጣል።


ሰባተኛውም መልአክ እምቢልታውን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት የጌታ የአምላካችንና የመሲሑ ሆናለች፤ እርሱ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤” የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ።


ከዚህ በኋላ አንድ ታላቅ ድምፅ ከሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “እነሆ አዳኝነት፥ ኀይል፥ መንግሥትም የአምላካችን ሆኖአል! ሥልጣንም የመሲሑ ሆኖአል! ወንድሞቻችንን በአምላካችን ፊት ቀንና ሌሊት ሲያሳጣቸው የነበረ የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos