እኔ ኢየሩሳሌምንና ሕዝብዋን እንዴት እንደምቀጣ በሰማህ ጊዜ፥ ራስህን አዋርደኽ በሐዘን ልብስህን በመቅደድና በማልቀስ ንስሓ ገብተሃል፤ ስለዚህ ጸሎትህን ሰምቼአለሁ።
መዝሙር 6:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ልመናዬን ያዳምጣል፤ እግዚአብሔር ለጸሎቴ መልስ ይሰጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ልመናዬን ሰምቷል፤ እግዚአብሔር ጸሎቴን ይቀበላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓመፃን የምታደርጉ ሁሉ፥ ከእኔ ራቁ፥ ጌታ የልቅሶዬን ቃል ሰምቶአልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ልመናዬን ሰማኝ፤ እግዚአብሔር ጸሎቴን ተቀበለ። |
እኔ ኢየሩሳሌምንና ሕዝብዋን እንዴት እንደምቀጣ በሰማህ ጊዜ፥ ራስህን አዋርደኽ በሐዘን ልብስህን በመቅደድና በማልቀስ ንስሓ ገብተሃል፤ ስለዚህ ጸሎትህን ሰምቼአለሁ።
“ወደ ሕዝቅያስ ሄደህ እንዲህ በለው፤ ‘እነሆ፥ የቀድሞ አባትህ የዳዊት አምላክ እኔ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰምቼአለሁ፤ እንባህንም አይቼአለሁ፤ ስለዚህም በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት ጨምሬልሃለሁ፤
“እግዚአብሔር ሆይ! ተጨንቄ ሳለሁ ወደ አንተ ተጣራሁ፤ አንተም መለስክልኝ፤ ርዳታህን ለማግኘት ጥልቅ ከሆነው ከሙታን ዓለም ወደ አንተ ጮኽኩ፤ አንተም ሰማኸኝ።