መዝሙር 54:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ጸሎቴን ስማ! ቃሌንም አድምጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማልኝ፤ የአፌንም ቃል አድምጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዜፋውያን መጥተው ለሳኦል፦ እነሆ ዳዊት በእኛ ዘንድ ተሸሽጓል ብለው በነገሩት ጊዜ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተመልከተኝ፥ ስማኝም፤ አዘንሁ፥ ደነገጥሁ፥ ተናወጥሁም፤ |
እግዚአብሔር ሆይ! መንፈሴ ስለ ዛለብኝ ፈጥነህ መልስ ስጠኝ! ፊትህን ከእኔ አትሰውርብኝ! አለበለዚያ ወደ ጥልቁ ጒድጓድ እንደሚወርዱት ሰዎች እሆናለሁ።
ከዚፍ ነዋሪዎች አንዳንዶቹ በጊብዓ ወደሚገኘው ወደ ሳኦል ሄደው እንዲህ አሉ፥ “ዳዊት በእኛ ግዛት ውስጥ ከይሁዳ ምድረ በዳ በስተ ደቡብ ባለው በሐኪላ ተራራ ላይ በምትገኘው በሖሬሽ ተሸሽጎ ይገኛል።
ጥቂት ሰዎች ከዚፍ ተነሥተው ሳኦል ወዳለበት ወደ ጊብዓ በመምጣት “እነሆ፥ ዳዊት ከይሁዳ ምድረ በዳ ዳርቻ በተለይ ሐኪላ ተብሎ በሚጠራው ተራራ ላይ ተደብቆ ይገኛል” ብለው ነገሩት፤