መዝሙር 52:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለሙ ያጠፋሃል፤ ከቤትህ አስወጥቶ ያባርርሃል። ከሕያዋንም ምድር ያስወግድሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ግን ለዘላለም ያንኰታኵትሃል፤ ይነጥቅሃል፤ ከድንኳንህም መንጥቆ ያወጣሃል፤ ከሕያዋንም ምድር ይነቅልሃል። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመልካም ይልቅ ክፋትን፥ ጽድቅንም ከመናገር ይልቅ ዓመፃን ወደድህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር የግብዞችን አጥንቶች በትኖአልና በዚያ የሚያስፈራ ሳይኖር እጅግ ፈሩ፤ እግዚአብሔር አዋርዶአቸዋልና አፈሩ። |
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ክፉዎችን ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ትጥላቸዋለህ፤ እነዚያ ነፍሰ ገዳዮችና ከዳተኞች ግማሽ ዕድሜአቸውን እንኳ አይኖሩም፤ እኔ ግን በአንተ እተማመናለሁ።
ነገር ግን ፈሪዎች፥ እምነተ ቢሶች፥ ርኩሶች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ አመንዝሮች፥ አስማተኞች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸታሞች ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲን በሚቃጠለው በእሳት ባሕር ውስጥ ይሆናል፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”