በደል ያልሠሩትን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህ ብዬ አላስብም፤ ይህንን እንደማታደርገው አምናለሁ፤ ይህንንማ ካደረግህ ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር መቀጣታቸው ነው፤ ይህ ከቶ አይሆንም! የዓለም ሁሉ ፈራጅ በትክክል መፍረድ ይገባው የለምን?”
መዝሙር 50:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ብቸኛ ዳኛ ስለ ሆነ ሰማያት የእርሱን ፍትሕ ያውጃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፤ እግዚአብሔር ራሱ ፈራጅ ነውና። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፥ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ እውነትን ወደድህ፤ የማይነገር ስውር ጥበብህን አስታወቅኸኝ። |
በደል ያልሠሩትን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህ ብዬ አላስብም፤ ይህንን እንደማታደርገው አምናለሁ፤ ይህንንማ ካደረግህ ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር መቀጣታቸው ነው፤ ይህ ከቶ አይሆንም! የዓለም ሁሉ ፈራጅ በትክክል መፍረድ ይገባው የለምን?”
እያንዳንዱ በምድራዊ ሕይወቱ ላደረገው ክፉም ሆነ ደግ ነገር እንደየሥራው ዋጋውን ለመቀበል ሁላችንም በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት መቅረብ አለብን።
ፍርዱ እውነትና ትክክል ነው፤ ምድርን በአመንዝራነትዋ ያረከሰችውን ታላቂቱን አመንዝራ በፍርድ ቀጥቶአታል፤ እርስዋን በመቅጣትም የአገልጋዮቹን ደም ተበቅሎአል።”