መዝሙር 50:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአተኛውን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፤ “ሕጌን ለማንበብ፥ ቃል ኪዳኔን በአንደበትህ ለመግለጽ ምን መብት አለህ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉውን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፤ “ሕጌን ለማነብነብ፣ ኪዳኔንም በአፍህ ለመናገር ምን መብት አለህ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉውን ግን እግዚአብሔር አለው፦ ለምን አንተ ሕጌን ትናገራለህ? ኪዳኔንም በአፍህ ለምን ትይዛለህ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አትወድድም። |
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ እኔንም የሚያመልከኝ ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን እያስተማረ በከንቱ ነው።
ይህም ቃል ኪዳን እጃቸውን ይዤ ከግብጽ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ቃል ኪዳን ያለ አይደለም፤ እነርሱ በቃል ኪዳኔ ስላልጸኑ እኔም ችላ አልኳቸው ይላል ጌታ።
እነርሱ የቀናውን መንገድ ትተው ጠፍተዋል፤ ክፉ በመሥራት የሚገኘውን ገንዘብ የወደደውን የቢዖርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከትለው ተሳስተዋል።