7 ሞኝ በምሳሌ የሚጠቀመው ሽባ ሰው በአንካሳ እግሮቹ የሚጠቀመውን ያኽል ነው።
7 በሞኝ አንደበት የሚነገር ምሳሌ፣ የሰለለ የሽባ ሰው እግር ነው።
7 በምሳሌ የሚናገር ሞኝ፥ እንደተንጠለጠሉ የአንካሳ እግሮች ነው።
የሞኝ በምሳሌ መናገር ሰካራም በእጁ ላይ የተሰካውን እሾኽ ለማውጣት እንደ መታገል ያለ ነው።
ሞኝ ሰው ቁም ነገር አይናገርም፤ ከጨዋ ሰው ግን የውሸት ንግግር አይጠበቅም።
እግዚአብሔር ንግግራቸው በራሳቸው ላይ ተመልሶ እንዲወድቁ ያደርጋቸዋል። የሚያዩአቸው ሁሉ በፍርሃት ከእነርሱ ይሸሻሉ።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ ‘አንተ ሐኪም፥ እስቲ ራስህን አድን፥’ የሚለውን ምሳሌ እንደምትጠቅሱብኝ እርግጠኛ ነኝ፤ እንዲሁም ‘በቅፍርናሆም አድርገሃል ሲሉ የሰማነውን ሁሉ፥ እዚህም በገዛ አገርህ አድርግ’ ትሉኛላችሁ።
ሞኝን መልእክተኛ ማድረግ የገዛ እግርን እንደ መቊረጥና ዐመፅን እንደ መጋበዝ ይቈጠራል።
ለሞኝ ክብርን መስጠት ድንጋይን በወንጭፍ ላይ አጥብቆ አስሮ ለመወንጨፍ እንደ መሞከር ነው።