እግዚአብሔር አምላክ ከምድር ዐፈር ወስዶ እንስሶችንና ወፎችን ሁሉ ፈጠረ፤ ምን ዐይነት ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም አመጣቸው፤ አዳም ለእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር ያወጣለት ስም መጠሪያው ሆነ።
መዝሙር 50:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዱር ያሉ አራዊትና በሺህ የሚቈጠሩ ተራራዎች ላይ የሚሰማሩት የእንስሶች መንጋዎች የእኔ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዱር አራዊት ሁሉ፣ በሺሕ ተራሮች ላይ ያለውም እንስሳ የእኔ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ በሺህ ተራራዎች ያሉ እንስሶችም የእኔ ናቸውና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። |
እግዚአብሔር አምላክ ከምድር ዐፈር ወስዶ እንስሶችንና ወፎችን ሁሉ ፈጠረ፤ ምን ዐይነት ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም አመጣቸው፤ አዳም ለእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር ያወጣለት ስም መጠሪያው ሆነ።
ተራብተውና ተባዝተው ምድርን ሁሉ እንዲሞሉ ከአንተ ጋር ያሉትን ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ወፎችን፥ እንስሶችንና ሌሎችን በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱትን ፍጥረቶች ሁሉ ይዘህ ውጣ።”
ሣርን ለእንስሶች ታበቅላለህ፤ አትክልትንም ለሰው ልጆች ጥቅም እንዲውል ታደርጋለህ፤ በዚህ ዐይነት ሰው ምግብ የሚሆነውን ዘርቶ ይሰበስባል።
ነነዌ ክፉና ደጉን የማይለዩ ከአንድ መቶ ኻያ ሺህ ሕዝብ በላይ የሚኖሩባት ከተማ ነች፤ ብዙ እንስሶችም አሉባት፤ ታዲያ እኔ ለዚህች ታላቂቱ ከተማ አልራራምን?”