እንዳይሞትና ወደ መቃብር እንዳይወርድ፥ ለዘለዓለም እንዲኖር ለማድረግ የቱንም ያኽል ቢከፈል በቂ አይሆንም።
በዚህም ዘላለም ይኖራል፣ መበስበስንም አያይም።
የነፍሳቸው ዋጋ ክቡር ነው፥ መቼውንም በቂ አይሆንም፥
ከቤትህ ፍሪዳን፥ ከመንጋህም ጊደርን አልወስድም፤
ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም፤ ታማኝህንም መበስበስ እንዲደርስበት አታደርግም።
ጌታ ሆይ! የተትረፈረፈ ሀብት ያላቸው ሁሉ ይሰግዱልሃል። ለሞትና ለመቃብር የተቃረቡትም መጥተው ይንበረከኩልሃል።
ሰው ሞት ሳይደርስበት እንዲሁ ለመኖር እንዴት ይችላል? ወደ መቃብር ሳይወርድ ሊቀርስ እንዴት ይችላል?
አግባብ ባልሆነ መንገድ የተገኘ ሀብት አይጠቅምም፤ ቀጥተኛነት ግን ከሞት ያድናል።
ለመሞት በምትቃረብበት ቀን ሀብትህ አይጠቅምህም፤ ደግነት ግን የሕይወት ዋስትና ይሆንልሃል።
የሕይወትን እስትንፋስ ለማስቀረትና የሞትን ቀን ለመለወጥ የሚችል ማንም የለም፤ ማንም ሰው ከጦር ሜዳ መሰናበት እንደማይችል ክፋትም ክፉ ሠሪዎችን አይለቃቸውም።
የቀድሞ አባቶቻችሁ አሁን የት አሉ? ነቢያቱስ ለዘለዓለም ይኖራሉን?
እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሞት በማስነሣቱ ይህንኑ ተስፋ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞታል፤ ይህም በሁለተኛው መዝሙር፥ ‘አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤’ ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።
ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም፤ ቅዱስህንም በመቃብር በስብሶ እንዲቀር አታደርገውም።
በዚህም ምክንያት መሲሕ በሲኦል እንደማይቀርና ሥጋውም በመቃብር በስብሶ እንደማይቀር አስቀድሞ አይቶ ስለ ትንሣኤው ተናገረ።