መዝሙር 45:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንቺ ልጄ ሆይ! የምልሽን ስሚ፤ ቃሌንም አድምጪ፤ ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጄ ሆይ፤ ስሚ፤ አስተውዪ፤ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፥ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልብ አድርጉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ። |
እነርሱም በመርከብ ተጒዘው ወደ ኦፊር ምድር ከሄዱ በኋላ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ሲመለሱ ከዐሥራ አራት ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን ወርቅ ይዘውለት መጡ።
ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ፥ የእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ፥ የእኔ ሊሆን አይገባውም።
ስለ እኔ ብሎ ቤቶችን፥ ወይም ወንድሞችን፥ ወይም እኅቶችን፥ ወይም አባትን ወይም እናትን፥ ወይም ልጆችን፥ ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል፤ የዘለዓለም ሕይወትንም ያገኛል።
“ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሕይወት እንኳ ከእኔ አብልጦ የሚወድ ከሆነ የእኔ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይችልም።
ከእንግዲህ ወዲህ እኛ ማንንም ሰው በሥጋዊ አመለካከት አንመለከትም፤ ከዚህ በፊት ክርስቶስንም የተመለከትነው እንደ ማንኛውም ሰው በሥጋዊ አመለካከት ከሆነ ለወደፊቱ ግን ይህን አናደርግም።
ልብስዋን ትለውጥ፤ እርስዋም ከአንተ ጋር በቤትህ ተቀምጣ እስከ አንድ ወር ድረስ በጦርነት ስለሞቱት ወላጆችዋ ታልቅስ፤ ከዚያም በኋላ ሚስት አድርገህ ታገባታለህ።