Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 9:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 እነርሱም በመርከብ ተጒዘው ወደ ኦፊር ምድር ከሄዱ በኋላ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ሲመለሱ ከዐሥራ አራት ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን ወርቅ ይዘውለት መጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 እነዚያም ወደ ኦፊር ሄደው አራት መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ይዘው ተመለሱ፤ ይህንም ወደ ንጉሥ ሰሎሞን አመጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 እነርሱም በመርከብ ተጉዘው ወደ ኦፊር ምድር ከሄዱ በኋላ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ሲመለሱ ከዐሥራ አራት ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን ወርቅ ይዘውለት መጡ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ወደ አፌ​ርም ደረሱ፤ ከዚ​ያም አራት መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ ወሰዱ፤ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎ​ሞ​ንም ይዘው አገቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ወደ ኦፊርም መጡ፤ ከዚያም አራት መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ወሰዱ፤ ወደ ንጉሡም ወደ ሰሎሞን ይዘው መጡ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 9:28
15 Referencias Cruzadas  

ኦፊር፥ ሐዊላና ዮባብ ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ዘሮች ናቸው።


ከኦፊር ወርቅ ያመጡለት የኪራም መርከቦች ከዚያው ከኦፊር ብዙ የሰንደል እንጨትና የከበረ ዕንቊ አምጥተውለት ነበር።


ንጉሥ ሰሎሞን በየዓመቱ ኻያ ሦስት ሺህ ኪሎ ያኽል የሚመዝን ወርቅ ያገኝ ነበር፤


ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ውቅያኖስን አቋርጠው ከኦፊር ወርቅ የሚያመጡለትን የተርሴስ ዐይነት መርከቦች አሠርቶ ነበር፤ ነገር ግን መርከቦቹ በኤጽዮንጋብር ወደብ ላይ ስለ ተሰበሩ መጓዝ አልቻሉም።


ከዚያም በኋላ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ መርከበኞቹ ከኢዮሣፍጥ መርከበኞች ጋር በኅብረት እንዲሠሩ የውል ድርድር አቅርቦ ነበር፤ ኢዮሣፍጥ ግን ሐሳቡን አልተቀበለም።


ኦፊርን፥ ሐዊላና ዮባብን ወለደ። እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ነበሩ።


በዚህ መሠረት መቶ ሺህ ኪሎ የኦፊር ወርቅና ሁለት መቶ አርባ ሺህ ኪሎ የሚሆን ንጹሕ ብር የቤተ መቅደሱን ግንቦች ለማስጌጥና፥


ንጉሥ ኪራም በሠለጠኑ መርከበኞች የሚነዱና በራሱ መኰንኖች የሚመሩ መርከቦችን ለሰሎሞን ልኮለት ነበር፤ እነርሱም ከሰሎሞን መኰንኖች ጋር በመሆን ወደ ኦፊር ምድር መጡ፤ ከዚያም ከዐሥራ አምስት ሺህ ኪሎ የሚበልጥ ወርቅ ለሰሎሞን ይዘውለት መጡ።


ከኦፊር ወርቅ ያመጡ የንጉሥ ኪራምና የንጉሥ ሰሎሞን ሰዎች ከዚያው ከኦፊር የሰንደል እንጨትና ዕንቊ ለሰሎሞን አምጥተውለት ነበር፤


ወርቅን ወደ ትቢያ ጣለው፤ የኦፊርንም ወርቅ እንደ ጅረት ድንጋይ ወርውረው፤


ጥበብ ኦፊር ከሚባል ወርቅና፥ መረግድና ሰንፔር ከሚባሉ ዕንቆች የከበረች ናት።


አንቺ ልጄ ሆይ! የምልሽን ስሚ፤ ቃሌንም አድምጪ፤ ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ።


በቤተ መንግሥትህ ከሚገኙት ወይዛዝርት መካከል፥ የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤ ንግሥቲቱም በንጹሕ ወርቅ ያሸበረቀ ጌጠኛ ልብስ ተጐናጽፋ ከዙፋንህ በስተቀኝ ቆማለች።


እኔ በምገዛው አገር ሁሉ ከልዩ ልዩ አውራጃዎች የከበሩ የቤተ መንግሥት መዛግብትን በመሰብሰብ ብዙ ወርቅና ብር አከማቸሁ፤ እኔን የሚያሞግሡ ወንዶችና ሴቶች አዝማሪዎችንም አዘጋጀሁ፤ ለሰው ተድላና ደስታን ሊሰጡ የሚችሉ እጅግ ብዙ ሴቶችንም ሰበሰብኩ።


ሰውን ከወርቅ ይልቅ፥ ከኦፌር ወርቅም የበለጠ ብርቅና ውድ አደርገዋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos