መዝሙር 44:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ንጉሤና አምላኬ ነህ፤ የያዕቆብ ዘር ለሆነው ሕዝብህ፥ ድልን የምታጐናጽፍ አንተ ነህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ንጉሤ ነህ፤ ያዕቆብም ድል እንዲያደርግ የወሰንህ አንተ ነህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰይፋቸው ምድርን አልወረሱም ክንዳቸውም አላዳናቸው፥ ቀኝህና ክንድህ የፊትህም ብርሃን ነው እንጂ፥ ወድደሃቸዋልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ቅንነትና ስለ የዋህነት ስለ ጽድቅም አቅና፥ ተከናወን፥ ንገሥም፤ ቀኝህም በክብር ይመራሃል። |
ኢየሱስም ሕዝቡ እየተራወጡ ሲመጡ አየ፤ ርኩሱንም መንፈስ “አንተ ድዳና ደንቆሮ መንፈስ ከልጁ እንድትወጣ ወደ እርሱም ተመልሰህ እንዳትገባ አዝሃለሁ!” ብሎ ገሠጸው።
በገዛ ዐይኖችህ ያየሃቸውን ታላላቅ መቅሠፍቶች፥ ተአምራትንና ድንቅ ሥራዎችን፥ እንዲሁም እግዚአብሔር አምላክህ አንተን ነጻ ያወጣበትን ታላቅ ኀይሉንና ሥልጣኑን አስታውስ፤ ግብጻውያንን ባጠፋበት ዐይነት ዛሬ አንተ የምትፈራቸውን እነዚህንም ሕዝቦች ሁሉ ያጠፋቸዋል።
ነገር ግን እግዚአብሔር እናንተን ስለ ወደደ ለቀድሞ አባቶቻችሁ የሰጠውን የተስፋ ቃል መጠበቅ ፈለገ፤ በታላቅ ኀይሉ ያዳናችሁና የግብጽ ንጉሥ ባርያዎች ከመሆን ነጻ ያወጣችሁም በዚህ ምክንያት ነበር።
በሁለቱ አሞራውያን ነገሥታት ላይ እንዳደረግሁት አስቀድሜ ከፊታችሁ ያባረራቸውን ተርብ ሰደድኩባቸው፤ ይህ በእናንተ ሰይፍ ወይም በእናንተ ቀስት የሆነ አይደለም።