መዝሙር 39:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ታዲያ፥ እኔ ተስፋዬን በአንተ ላይ ከማድረግ በቀር ሌላ ምን እጠብቃለሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጌታ ሆይ፤ አሁንስ ወደ ማን ልመልከት? ተስፋዬ በአንተ ላይ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእውነት ሰው እንደ ጥላ ይመላለሳል፥ በእውነት በከንቱ ይታወካል። ያከማቻል የሚሰበስብለትንም አያውቅም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜ አልሁ፥ “እነሆ፥ መጣሁ፤ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል፤ |
ባለህ ጥበብ፥ በቀሰምከውም ዕውቀትና ብልኀት የለፋህበትን ሁሉ ምንም ላልደከመበት ሰው ትተህለት ታልፋለህ፤ ይህም ከንቱ ስለ ሆነ ታላቅ መከራ ነው።
እነሆ፥ ብቻውን የሚኖር አንድ ሰው አለ፤ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፤ ይሁን እንጂ ዘወትር በሥራ ከመድከም አይቦዝንም፤ ባገኘውም ሀብት በቃኝ ማለትን አላወቀም፤ “እርሱም የምደክመው ለማን ነው? ለራሴስ ደስታን የምነፍገው ለምንድን ነው?” ብሎ ራሱን ይጠይቃል፤ ይህ ሁሉ የባሰ ከንቱና የሥቃይ ሕይወት ነው።
በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ሕይወቱን ለእግዚአብሔር የሰጠ ጻድቅ ሰው ነበር፤ የእስራኤልን የመዳን ተስፋ ይጠባበቅ ነበር፤ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበር።