ሰውን በኃጢአቱ ትገሥጸዋለህ፤ ትቀጣዋለህም፤ የሚወደውንም ነገር እንደ ብል ታጠፋበታለህ፤ በእርግጥ ሰው ከነፋስ ሽውታ የሚሻል አይደለም።
ሰዎችን ስለ ኀጢአታቸው ለመቅጣት ትገሥጻቸዋለህ፤ ሀብታቸውንም ብል እንደ በላው ታደርጋለህ፤ በርግጥ ሰው ሁሉ ተን ብቻ ነው። ሴላ
መቅሠፍትህን ከእኔ አርቅ፥ ከእጅህ ብርታት የተነሣ አልቄአለሁና።
አቤቱ አንተ ይቅርታህን ከእኔ አታርቅ፤ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ያግኙኝ።
ከዚህ የተነሣ እኔ እንደ በሰበሰ ነገር ሆኜ እቀራለሁ፤ ብል እንደ በላውም ልብስ እጠፋለሁ።
ቆዳዬ ጠቊሮ ተገለፈፈ፤ ሰውነቴም በትኩሳት ተቃጠለ።
ታዲያ፥ ምስጥ ሳይበላቸው የሚፈርሱ መሠረታቸው ዐፈር በሆነና ከሸክላ በተሠራ ቤት ውስጥ በሚኖሩትማ ላይ እንዴት ይተማመንባቸዋል?
የሚረዳኝ ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ ማን ይፈርድብኛል? ከሳሾቼ እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ ብልም ይበላቸዋል።
ስለዚህ ብልና ነቀዝ እህልንና እንጨትን እንደሚያጠፉ እኔም እስራኤልንና ይሁዳን አጠፋለሁ።
በኃጢአት የተሞላው የዚህ ሰው ሥጋ ይፈርስ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፋችሁ ልትሰጡት ይገባል። ይህንንም የምታደርጉት ጌታ ኢየሱስ ለፍርድ በሚመጣበት ቀን የዚህ ሰው ነፍስ እንድትድን ነው።
ጌታ የሚወደውን ይገሥጻል፤ እንደ ልጁ አድርጎ የሚያየውንም ይቀጣል።”
በለዓም ግን ስለ ኃጢአቱ ተገሥጾአል፤ መናገር የማትችል አህያ በሰው ቃል ተናግራ የነቢዩን የእብደት ሥራ ተቃውማለች።
እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸዋለሁም፤ ስለዚህ ትጋ፤ ንስሓም ግባ፤