La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 35:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አነጋገራቸው የጠላት አነጋገር ነው፤ በሰላማዊ ሰው ላይ ተንኰልን ያቅዳሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሰላም ንግግር ከአፋቸው አይወጣም፤ ዳሩ ግን በምድሪቱ በጸጥታ በሚኖሩት ላይ፣ ነገር ይሸርባሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በእርጋታ በምድሪቱ ለተቀመጡት ሰላምን አይናገሩምና፥ በቁጣም ሽንገላን ይመክራሉ።

Ver Capítulo



መዝሙር 35:20
15 Referencias Cruzadas  

የብዙ ሰዎችን ሹክሹክታ እሰማለሁ፤ በሁሉም አቅጣጫ ፍርሀት አለ፤ በእኔ ላይ ያሤራሉ፤ ሊገድሉኝ በማቀድ ያድማሉ።


ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ወጥመድ ይዘረጉብኛል፤ ሊጐዱኝ የሚያቅዱ ሊያጠፉኝ ይዝታሉ፤ በእኔም ላይ ቀኑን ሙሉ ያሤራሉ።


አንተ ተንኰለኛ ጥፋትህን ታሤራለህ፤ አንደበትህ እንደ ተሳለ ምላጭ ነው።


ወደ ዕርድ እንደሚሄድ የበግ ጠቦት ሆኜ ነበር፤ እነርሱ “ስሙ ዳግመኛ እንዳይታወስ ዛፉን ከነፍሬው እናጥፋ፤ ከሕያዋያን ዓለም እናስወግደው” ብለው በእኔ ላይ ማደማቸውን አላወቅሁም ነበር።


ስለዚህም እርስ በርሳቸው “ከአምላኩ ሕግ በቀር ዳንኤልን የምንከስበት ምንም ዐይነት በደል ማግኘት አልቻልንም” ተባባሉ።


እርሱ አይከራከርም ወይም አይጮኽም፤ በመንገዶችም ላይ ድምፁን የሚሰማ የለም።


ፈሪሳውያን ግን ይህን በሰሙ ጊዜ “እርሱ ‘ብዔልዜቡል’ በተባለው በአጋንንት አለቃ አማካይነት ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም” አሉ።


እዚያም ኢየሱስን በተንኰል ለመያዝና ለመግደል አሤሩ።


ስለዚህ እናንተ ከሸንጎው ጋር ተስማምታችሁ በጥብቅ የምትመረምሩት ነገር እንዳለ በማስመሰል ጳውሎስን እንዲያመጡላችሁ አዛዡን ጠይቁት፤ እኛም እዚህ ከመድረሱ በፊት ልንገድለው ተዘጋጅተናል።”