እኔን ከጒዳት ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እነርሱንም ይጠብቃቸው። የእኔ ስም፥ የአባቶቼም የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በነዚህ ልጆች ሲታወስ ይኑር፤ ዘራቸውም በምድር ላይ ይብዛ።”
መዝሙር 34:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔርን ደግነት እዩና ቅመሱ፤ እርሱን ከለላ ያደረገ የተባረከ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እዩ፤ እርሱን መጠጊያ የሚያደርግ ምንኛ ብፁዕ ነው! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ መልአክ ጌታን በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያላወቋት ወጥመድ ትምጣባቸው፥ የሸሸጓትም ወጥመድ ትያዛቸው፤ በዚህችም ወጥመድ ውስጥ ይውደቁ። |
እኔን ከጒዳት ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እነርሱንም ይጠብቃቸው። የእኔ ስም፥ የአባቶቼም የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በነዚህ ልጆች ሲታወስ ይኑር፤ ዘራቸውም በምድር ላይ ይብዛ።”
አንተ ብርቱ ሰው፥ በእግዚአብሔር ወገኖች ላይ ክፉ ነገር በማድረግ የእግዚአብሔር ፍቅር ዘለዓለማዊ መሆኑን እያወቅህስ ስለምን ዘወትር ትመካለህ?
ውዴ ከሌሎች ጐልማሶች ጋር ሲነጻጸር በዱር ዛፎች መካከል አምሮ እንደሚታይ የፖም ዛፍ ነው፤ እኔም እጅግ ደስ ብሎኝ በጥላው ሥር ዐረፍኩ፤ ጣፋጭ ፍሬውንም በመመገብ ተደሰትኩ።
እኅቴ ሙሽራዬ ሆይ! እነሆ ወደ አትክልት ቦታዬ ገባሁ፤ ከርቤዬንና የሽቶ አበባዎቼን ለቀምኩ፤ የማር ሰፈፌን ከወለላው ጋር ተመገብኩ፤ የወይን ጠጄንና ወተቴንም ጠጣሁ። ወዳጆቼ ሆይ! በፍቅር እስክትረኩ ድረስ ብሉ፥ ጠጡ።
ከዚህም በኋላ ንጉሡ ናቡከደነፆር እንዲህ አለ፦ “የሲድራቅ፥ የሚሳቅና የአብደናጎ አምላክ የተመሰገነ ይሁን! እርሱ መልአኩን ልኮ እነዚህን አገልጋዮቹን አድኖአል፤ እነርሱ በአምላካቸው ተማምነው ለእርሱ ካልሆነ በቀር ለሌሎች አማልክት አንሰግድም በማለት የንጉሡን ትእዛዝ በማፍረስ ሕይወታቸውን በአደጋ ላይ ጥለውት ነበር።