የአንበሳ ደቦሎች ያጣሉ፤ ይራባሉም፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ምንም አይጐድልባቸውም፤ መልካም ነገርም አያጡም።
አንበሶች ሊያጡ፣ ሊራቡም ይችላሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጐድልባቸውም።
የሚፈሩት ምንም አያጡምና ቅዱሳኑ ሁሉ፥ ጌታን ፍሩት።
አጥንቶች ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፦ “አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? ድሃውን ከሚቀማው እጅ ድሃውንና ችግረኛውንም ከሚነጥቀው እጅ ታድነዋለህ።”
እግዚአብሔር የሚያዘጋጀውን ምግብ ሲያድኑ የአንበሳ ደቦሎች ያገሣሉ።
ቤተሰቦቹ ሀብታሞችና ባለጸጎች ይሆናሉ፤ ጽድቅም ለዘለዓለም የእርሱ ይሆናል።
እግዚአብሔር እረኛዬ ስለ ሆነ፥ የሚያስፈልገኝን ሁሉ አላጣም።
ይህም የሚሆነው ከሞት ሊያድናቸውና ከራብም ሊጠብቃቸው ነው።
ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ እንደ ፀሐይና እንደ ጋሻ ነህ፤ በቸርነትና በክብር ትጠብቀናለህ፤ ደግ ለሚሠሩ ሰዎች ማናቸውንም መልካም ነገር አትከለክላቸውም።
እግዚአብሔር ደጋግ ሰዎችን እንዲራቡ አያደርግም፤ ክፉዎች ግን የተመኙትን እንዳያገኙ ያደርጋል።
እግዚአብሔርን ብትፈራ ረጅም ዕድሜ ይኖርሃል፤ ጒዳት ሳይደርስብህ በደስታና በሰላም ትኖራለህ።
እግዚአብሔርን መፍራትና ትሑት መሆን ሀብት፥ ክብርና ሕይወትን ያስገኛል።
ይህን ለማግኘትማ አሕዛብም ይፈልጋሉ፤ እናንተ ይህ ሁሉ እንደሚያስፈልጋችሁ፥ የሰማይ አባታችሁ ያውቃል።