መዝሙር 29:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነው፤ ድምፁም ባለ ግርማ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነው፤ የእግዚአብሔር ድምፅ ግርማዊ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ድምፅ በኃይል ነው፥ የጌታ ድምፅ በታላቅ ክብር የተሞላ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቃን ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ። |
እግዚአብሔር ክቡር ድምፁን እንዲሰሙ ያደርጋል። በኀይለኛ ቊጣው፥ በሚያቃጥል የእሳት ነበልባል፥ በመብረቅ፥ በወጀብና በጠጣር በረዶ የሚወርደው ኀይለኛ ቅጣቱ እንዲታይ ያደርጋል።
በከተማ የሚሰማውን ሁካታ አድምጡ! ከቤተ መቅደስም ድምፅ ስሙ፤ ይህም እኔ እግዚአብሔር ለጠላቶቼ ተገቢ ዋጋቸውን በምሰጥበት ጊዜ የሚሰማ ድምፅ ነው።”
ኪሩቤል በክንፎቻቸው የሚያሰሙት ድምፅ በውጪ በኩል ባለው አደባባይ እንኳ ይሰማ ነበር፤ ድምፁም ሁሉን የሚችል አምላክ ድምፅ ይመስል ነበር።
አሞጽ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ሆኖ እንደሚያገሣ አንበሳ የሚያስፈራ ድምፁን ያሰማል፤ ቃሉም ከኢየሩሳሌም ያስተጋባል፤ እረኞች መንጋ የሚያሰማሩበት መስክ ይጠወልጋል፤ በቀርሜሎስ ተራራ የሚገኘውም ልምላሜ ይደርቃል።”
ሁሉም በመደነቅ እርስ በርሳቸው፥ “ይህ ምን ዐይነት ቃል ነው? በሥልጣንና በኀይል ርኩሳን መናፍስትን ያዛል፤ እነርሱም ታዘው ይወጣሉ፤” ተባባሉ።
ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፥ “እምነታችሁ የት አለ?” አላቸው። እነርሱ ግን እጅግ ተደንቀውና ፈርተው እርስ በርሳቸው፥ “ነፋስንና ማዕበልን ያዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታል፤ ለመሆኑ ይህ ማን ነው?” ተባባሉ።