እዚያም በመላው ጉባኤ ፊት ንጉሥ ዳዊት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ እንዲህም አለ፦ “የቀድሞ አባታችን የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የተመሰገንክ ሁን!
መዝሙር 22:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድኾች እስኪጠግቡ ይበላሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹት ያመሰግኑታል፤ ልባቸው በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ይደሰታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምስኪኖች በልተው ይጠግባሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹትም ያመሰግኑታል፤ ልባችሁም ለዘላለም ሕያው ይሁን! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በታላቅ ጉባኤ ምስጋናዬ ከአንተ ዘንድ ነው። እርሱን በሚፈሩት ፊት ስእለቴን እሰጣለሁ። |
እዚያም በመላው ጉባኤ ፊት ንጉሥ ዳዊት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ እንዲህም አለ፦ “የቀድሞ አባታችን የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የተመሰገንክ ሁን!
ደግነትህን በልቤ ውስጥ አልደብቅም፤ ስለ ታማኝነትህና ስለ አዳኝነትህ ተናግሬአለሁ፤ ከትልቁ ጉባኤ ዘለዓለማዊ ፍቅርህንና እውነተኛነትህን አልሰውርም።
የሠራዊት አምላክ በዚህች በጽዮን ተራራ ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል፤ በግብዣውም ላይ ምርጥ የወይን ጠጅና፥ የተሟላ ምግብ ይዘጋጃል።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አገልጋዮቼ ይበላሉ፤ እናንተ ግን ትራባላችሁ፤ አገልጋዮቼ ይጠጣሉ እናንተ ግን ትጠማላችሁ፤ አገልጋዮቼ ይደሰታሉ፤ እናንተ ግን ኀፍረት ይደርስባችኋል።
እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ለዘለዓለም ከቶ አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ፥ ለሚጠጣው ሰው ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል።”