መዝሙር 21:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዘለዓለም በረከትን ሰጠኸው፤ አንተም ከእርሱ ጋር በመገኘትህ ደስ ታሰኘዋለህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘላለማዊ በረከትን ሰጠኸው፤ ከአንተ ዘንድ በሚገኝ ፍሥሓም ደስ አሠኘኸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው፥ ሞገስንና ግርማን በላዩ አኖርህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን ትል ነኝ፥ ሰውም አይደለሁም፤ በሰው ዘንድ የተናቅሁ፥ በሕዝብም ዘንድ የተዋረድሁ ነኝ። |
በሄድክበት ስፍራ ሁሉ እኔ ከአንተ ጋር ነበርኩ፤ ወደፊትም በተራመድህ መጠን ጠላቶችህን ድል አደረግሁልህ፤ ገና ደግሞ በዓለም እንደ ታወቁት ታላላቅ መሪዎች ዝነኛ አደርግሃለሁ።
ስለዚህ በፊትህ ለዘለዓለም ይኖር ዘንድ የእኔን የባሪያህን ቤት እንድትባርክ ፈቃድህ ይሁን፤ ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ቤተሰቤን ባርከኸዋል፤ እርሱም ለዘለዓለም የተባረከ ይሆናል።”
አምላክ ሆይ! ከዚያም በኋላ ለአንተ ለምታስደስተኝ ወደ መሠዊያህ ሄጄ እሰግድልሃለሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ በገናዬን እየደረደርኩ አመሰግንሃለሁ።
አንተ መልካሙን ነገር ትወዳለህ፤ ክፉውን ነገር ትጠላለህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ መረጠህ፤ ከሌሎች ነገሥታትም ይበልጥ የደስታን ዘይት ቀባህ።
ስለዚህ እግዚአብሔር ልጁን የላከው በመጀመሪያ ለእናንተ ነበር፤ ይህንንም ያደረገው እያንዳንዳችሁን ከክፉ መንገዳችሁ በመመለስ እንዲባርካችሁ ነው።”
ይህም የሆነው እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው በረከት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ለአሕዛብ እንዲደርስና እኛም እግዚአብሔር እሰጣችኋለሁ ያለውን መንፈስ ቅዱስን በእምነት እንድንቀበል ነው።