መዝሙር 18:50 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ላነገሠው ንጉሥ ታላቅ ድልን ያጐናጽፈዋል፤ ራሱ ለቀባው ዘለዓለማዊ ፍቅሩን ያሳየዋል፤ ለዳዊትና ለዘሩ ለዘለዓለም ይህን ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ላነገሠው ታላላቅ ድሎችን ይሰጣል፤ ጽኑ ፍቅሩንም ለቀባው፣ ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም ይገልጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ስለዚህ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥ ለስምህም እዘምራለሁ። |
ስለዚህ በፊትህ ለዘለዓለም ይኖር ዘንድ የእኔን የባሪያህን ቤት እንድትባርክ ፈቃድህ ይሁን፤ ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ቤተሰቤን ባርከኸዋል፤ እርሱም ለዘለዓለም የተባረከ ይሆናል።”
እግዚአብሔርም ለአብርሃምና ለዘሩ የተስፋ ቃል የሰጠው በዚህ ዐይነት ነው፤ መጽሐፍ የተስፋ ቃል ከአብርሃም በኋላ የተሰጠው ለብዙዎች እንደ ሆነ አድርጎ “ለዘሮችህ” አይልም፤ ነገር ግን ለአንድ እንደ ሆነ አድርጎ “ለዘርህ” ይላል፤ ይህም “ዘርህ” የተባለው ክርስቶስ ነው።
እግዚአብሔር ሳሙኤልን እንዲህ አለው፤ “ከንጉሥነት ስለ ሻርኩት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ድረስ ነው? እኔ እርሱ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ ይኖር ዘንድ አልፈልገውም። ይልቅስ የወይራ ዘይት በቀንድ ሞልተህ በመያዝ በቤተልሔም ወደሚኖረው እሴይ ተብሎ ወደሚጠራው ሰው ዘንድ ሂድ፤ እኔ ከእርሱ ልጆች መካከል አንዱን ንጉሥ እንዲሆን መርጬአለሁ።”
እግዚአብሔርን የሚቃወሙ ይደመሰሳሉ፤ ከሰማይም ያንጐደጒድባቸዋል፤ እግዚአብሔር በዓለም ሁሉ ይፈርዳል፤ ለንጉሥም ኀይልን ይሰጠዋል፤ ለመረጠውም ክብሩን ከፍ ከፍ ያደርግለታል።”